ነነዌ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ነነዌ
(ናይኑዋ)
Adad gate exterior entrance north3.JPG
የታደሰው አዳድ በር ፍርስራሽ
ሥፍራ
ነነዌ is located in መስጴጦምያ
{{{alt}}}
መንግሥት የአሦር መንግሥት
ዘመን ከ2380 እስከ 620 ዓክልበ.
ዘመናዊ አገር ኢራቅ
ጥንታዊ አገር አሦር

ነነዌአሦር ጥንታዊ ከተማ ነበረ። ፍርስራሹ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቅ ዳርቻ በሞሱል ዙሪያ አሁን አለ።

ኦሪት ዘፍጥረት 10፡11 መሠረት የሴም ልጅ አሦርሰናዖር ወጥቶ ነነዌንና ሌሎችን ከተሞች ሠራ። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ግን ከፊተኛው ቁጥር ከ10፡10 በመውሰድ አድራጊው እንደ ናምሩድ ቆጥረውት፣ ናምሩድ እራሱ ወደ አሦር (ወደ ሀገሩ) ወጥቶ እኚህን ከተሞች እንደ ሠራ ይላሉ። በጥንታዊ የግሪክ ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ ኒኑስ የነነዌ መስራችና የአሦር መጀመርያ ንጉስ ነበረ።

ነነዌ ከጥንት ጀምሮ ከአሹር ከተማ-አገር ይገዛ ነበር። እንደ አሹር ከ1440 እስከ 1366 ዓክልበ. ድረስ በሚታኒ ይቆጣጠር ነበር። ትልቅ ከተማ ነበረ። በ713 ዓክልበ. ንጉሥ ሰናክሬም የአሦርን ዋና ከተማ ወደ ነነዌ መለሠው።

ዋቢ መጽሐፍት [ለማስተካከል]