«የ1812 መቅድም»

ከውክፔዲያ


«የ1812 መቅድም»ኦፔራ ጓድ በፕዮትር ኢልዪች ቻይኮቭስኪ የተጻፈ ሙዚቃ ነው። ፈረንሳዮች1804 ዓ.ም. (1812 እ.ኤ.አ.) ወደ ሩሲያ በወረሩበት ወቅት የናፖሊዎን ሠራዊት ድል ስለሆነ ሙዚቃው ለጦርነቱ መታሠቢያ እንዲሆን ተጻፈ። ሙዚቃው በተለይ የሚታወቅበት የመድፍ ትኩስ ቅድም ተከተል በውስጡ ሊሰማ ስለሚችል ነው። አንዳንዴም የሙዚቃ ጓድ ሲያጫውተው በዕውነተኛ መድፍ ነው የሚደረገው። ምንም እንኳን በ1804 (1812) በአሜሪካ እና በእንግሊዝ መካከል ስለ ተዋገው ጦርነት ሙዚቃው አንዳችም ግንኙነት ባይኖረውም፣ በዩናይትድ ስቴት ውስጥ ብዙ ጊዜ እንደ አርበኞች ሙዚቃ ተቆጥሮ ይሰማል።