ሀመር

ከውክፔዲያ
ሀመር
ይህ መጣጥፍ ስለ ብሔሩ ነው። ለሌሎች ትርጉሞች፣ ሐመር (መንታ መንገድ) ይዩ።

ሀመር ወይም ሐመርኢትዮጵያ ብሔር ነው።

ቋንቋ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሐመሮች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን ‹‹ሐመር አፎ›› በማለት የሚጠሩ ሲሆን፣ ሌሎች ግን ‹‹ሐመርኛ›› ይሉታል። ቋንቋው በኦሞአዊ የቋንቋ ቤተሰብ ሥር ይመደባል። የብሔረሰቡ አባላት ከራሳቸው ቋንቋ በተጨማሪ የበና፣ የአርቦሬ፣ የካራ እና የዳሰነች ብሔረሰቦች ቋንቋዎችን በሁለተኛ ደረጃ የናገራሉ። የሐመር ቋንቋ ከንግግር ወይንም ከመግባባቢያነት አልፎ የትምህርት ወይም የሥራ ቋንቋ ለመሆን አልበቃም።

ሕዝብ ቁጥር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ1999 ዓ.ም በተደረገ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት መሠረት የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 46ሺ532 ነው፡፡

መልክዓ ምድር

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሐመር ብሔረሰብ በደቡብ ኦሞ ዞን ውስቅ ከሚገኙ ብሔረሰቦች አንዱ ሲሆን በዋናነት በዞኑ ውስጥ በሐመር ወረዳ ይኖራል፡፡ ‹‹ሐመር›› የሚለው ቃል የብሐረሰቡ መጠሪያ ቃል በብሔረሰቡ ቋንቋ ‹‹በተራራ እና በድንጋይ መካከል የሚኖሩ፣ የተዋሃዱና የተቀላቀሉ ሕዝቦች›› የሚል ፍቺ እንዳለውና ይህም ትርጉም ታሪካዊ መሠት እንደያዘ ከብሔረሰቡ አዛውንቶች የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ትውፊት ሐመሮች በጥንት ዘመን በትላልቅና ሰንሰለታማ ተራሮች መካከል የሚገኙ የተቦረቦሩ ቋጥኞች ውስጥ ይኖሩ እንደነበር የሚያመላክት እንደሆነ እንዚህ የዕድሜ ባለፀጋዎች ይናገራሉ፡፡ የብሔረሰቡ አባላት ዋነኛ መተዳደሪያ ከብት እርባታ ሲሆን፣ ከዚህ ጐን ለጐን ንብ በማነብ እና በዝቅተኛ ደረጃ ደግሞ በቆሎና ማሽላ ለዕለት ፍጆታ በማምረት ኑሮአቸውን ይመራሉ፡፡ የብሔረሰቡ ታሪካዊ አመጣጥ ጥንት ከ ‹‹ካራ››፣ ከ‹‹ኦሪ›› እና ከ‹‹መርሲ›› በመጡ የተለያዩ ማኀበራዊ ቡድኖች ውህደት የዛሬው የሐመር ብሔረሰብ እንደተገኘ ከብሔረሰቡ ታዋቂ ግለሰቦችና የሀገር ሽማግሌዎች የተገኘ አፍአዊ መረጃ ያስረዳል፡፡ ከእዚህ የትውፊት መረጃ እና ከላይ የተጠቀሱትን አራት መነሻ ሥፍራዎች መሠረት በማድረግ ብሔረሰቡ ውስጥ ስድስት ማኀበራዊ ቡድኖች መኖራቸውን ይናገራል፡፡ ‹‹ቶርቶሮ›› የሐመር ብሔረሰብ አባላት በአመት አንድ ጊዜ አደባባይ በመውጣት የሚያከብሩት ባህላዊ በዓላቸው ነው፡፡ የሚከበረውም በሰኔ ወር መባቻ በእሸት ወቅት ነው፡፡ በዓለም በድግስና በጭፈራ ይከበራል፡፡ የጭፈራው ዋነኛ ተዋናዮችም ያገቡ ወጣቶች ጎልማሶችና አዛውንቶች ሲሆኑ ፣ ያላገቡ ወጣቶችና ኮረዶች ሚና ደግሞ ድግሱን በማዘጋጀትና በማስተናገድ ላይ ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ ‹‹ኢቫንጋዲ ›› የሐመር ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች ብቻ የሚሳትፉበት ባህላዊ ጭፈራ ነው፡፡ ጭፈራውም በየሦስት ቀን አንዴ እያሰለሰ በሐመር መንደሮች በምሽት ጨረቃ ይካሄዳል፡፡ ‹‹ኢቫንጋዲ›› በአዝመራ ወቅት በሥራ የደከመን አእምሮና አካል ለማዝናናት ሲባል የሚደረግ ባህላዊ ጭፈራ ሲሆን፣ የሐመር ወጣቶች ከማኀበራዊ ሕይወት ጋር የሚተዋወቁበት አዳዲስ ባህላዊ ዘፈኖችና ጭፈራሲሆን፣ የሐመር ወጣቶች ከማኀበራዊ ሕይወት ጋር የሚተዋወቁበት አዳዲስ ባህላዊ ዘፈኖችና የአጨፋፈር ስልቶችን የሚቀስሙበት አጋጣሚ ነው፡፡ ከእዚህ በተጨማሪ ሐመሮች የተለያዩ አጋጣሚዎችን ምክንያት በማድረግ የሚጫወቱት ‹‹ኤሬ›› የተባለ ባህላዊ ጨዋታ አላቸው፡፡ ኤሬ ወደ ሌላ አካባቢ ወይም ወደ ዘመቻ ለመሄድ ሲታሰብ በፉከራ መልክ የሚከወን ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡ የሐመሮች ባህላዊ ቤት ከእንጨት የሚሠራ ሲሆን፣ ጣሪያው በሣር ይከደናል፡፡ ትኋንና ምስት ለመከላከል በሚል ግድግዳው በምንም አይመረግም፡፡ ባህላዊ ቤቱ የውስጥ ክፍሎች የሌሉት ልቅ በመሆኑ የቤት ውስጥ የመገልገያ ቁሳቁስ ከቆጥ ላይ ይሰቀላሉ፡፡ በቤት ግንባታው ሂደት ዋነኛውን ሚና የሚጫወቱት ወንዶች ሲሆኑ፣ ሴቶች ደግሞ በሣር አቅርቦት ይሳተፋሉ፡፡ ‹‹ሙና መቱቆ›› /ኩርኩፋ/፣ ‹‹ በላሽ›› /በማሽላ ቂጣ/፣ ‹‹ዳንጵደ›› (ፎሰሴ) እና (ዝጉ) (ከማሽላና ከበቆሎ የሚዘጋጅ ቂጣ) ዋነኛ የሐመሮች ባህላዊ ምግቦች ናቸው፡፡ ‹‹ፐርሴ›› (ቦርዴ) እና ‹‹አላ›› (የማር ብርዝ) ደግሞ ባህላዊ መጠጦቻቸው ናቸው፡፡ የአመጋገብ ሥርዓታቸውን በተመለከተ የቤቱ አባወራ ከሁሉም ቀድሞ ይመገባል ፡፡ እናት በመጨረሻ ለብቻዋ የምትመገብ ሲሆን፣ አንዳንዴም ከልጆቿ ጋር ትመገባለች፡፡ ሆኖም ግን አባወራው በምንም አጋጣሚ ከመጀመሪያ ወንድ ልጁ ጋር አይመገብም ይህን እንዳይፈጽም ባህላዊ ሥርዓቱ እንደሚከለከለው የብሔረሰቡ አዛውንቶች ይናገራሉ፡፡ የሐመር ልጆች በተለይም ሴቶች ሀፍረተ ሥጋቸውን ለመሸፈን ሲሉ ከቆዳ የሚዘጋጅና በሐመርኛ ‹‹ሺራን›› የሚባል ግልድም ያገለድማሉ፡፡ ከላይ ደረታቸውን ለመሸፈን ደግሞ ጥብቆ ‹‹ቃሼ›› ያጠልቃሉ፡፡ ሴቶች በዕድሜ ከፍ ሲሉ ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ‹‹ቶቆ›› ከወደ መቀመጫቸው ደግሞ ‹‹ፋላንቲ›› የተሰኘ ከቆዳ የሚዘጋጅ ባለ ጥንድ ጉርድ ቀሚስ ይለብሳሉ፡፡ ካገቡ በኋላ ደግሞ ከወገብ በታች ማለትም በፊት ለፊት ‹‹ኢኮርባ›› ከኋላ ‹‹ቡድኮርባ ›› የሚባል ከፍየል ቆዳ የተዘጋጀ ጥንድ ቀሚስ ይለብሳሉ፡፡ ከወገብ በላይ ደግሞ ‹‹ቃሼ›› ጥብቆ ያጠልቃሉ፡፡

ታዋቂ ሰዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]