ንብ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
የማር ንብ ወይም ሳይንሳዊ ስሟ Apis mellifera በመቅሰም ላይ

ንቦች በራሪ ነፍሳት (ሶስት አፅቂዎች) ሲሆኑ እንደ ጉንዳን ካሉ የHymenoptera ቤተሰቦች ይመደባሉ። እነዚህ ነፍሳት በተለይ በማር እና ሰም ምርታቸው ይታወቃሉ። በምድራችን ላይ ከ20,000 በላይ የታወቁ የንብ ዝርያዎች ሲኖሩ እነዚህም በ9 ታዋቂ ቤተሰቦች ተከፋፍለዋል። ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ ዝርያዎች ሊኖሯቸውም ይችላል። እነዚህ ነፍሳት በሁሉም አህጉራት (አንታርክቲካን ሳይጨምር ማለት ነው) ለነፍሳት የሚሆኑ አበባዎች ባሉበት ሁሉ ይገኛሉ።

«የንብ አካላቷ በሦስት ክፍል ይከፈላል። በአንደኛው ክፍል የምታሸትበትና የምትዳስስበት፤ የምትሰግበትም በግንባሯ በስተቀኝና በስተግራ ሁለት ቀጫጭን ነገሮች እንደ ቀንድ የሆኑ አሏት። ደግሞ በዚህ በገጿ ላይ ሁለት ትልልቅ ጠፍጣፋ ዓይኖች በግራና በቀኝ ሆነው ለማየት የሚያስችሏት በሌሎች ትንንሽ ዓይኖች የተሞሉ አሏት። በሁለተኛው ያካላት ክፍሏ ፀጉራሞች የሆኑ በአበባ ውስጥ ያለውን ኔክታር (ፈሳሽ ነገር) ስትመጥ የአበባ ዱቄት የምታመጣባቸው ስድስት እግሮች፣ ሁለት ወፈር ያሉ ክንፎችና ሌሎች ሁለት ሳሳ ያሉ ክንፎች በጠንካሮች ሥር የሆኑ አሏት። በሦስተኛው የአካላት ክፍሏ እንደ አንጓ ክርክር ያላቸው መተንፈሻዎች የምትነድፍበትና የተበላሸውን የምታስወጣበት አሏት።»[1]

ማጣቀሻ እና ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ ተክለማርያም ፈንታዬ፤ "ኆኀተ ጥበብ ዘ ሥነ ጽሑፍ"፤ ፲፱፻፷፬ ዓ/ም፦ ሪፕርተር፣ ፌርማታ (ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም)