አላህ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ

አላህ (በአረብኛالله) መደበኛ የሆነ ቃል ሲሆን የሚወክለውም ፈጣሪ ነው። ትርጉሙም «አምልኮ የሚገባው» ማለት ነው። በአብዛኛው ጊዜ የእስልምና እምነት ተከታዮች የአምላካቸው መጠሪያ ተደርጎ ሲወሰድ፣ የአረብኛ ተናጋሪ የሆኑት ሌሎች አብራሃማዊ አማኞች (በተለይ በክርስትናአይሁድና) ለጌታቸው መጠሪያ ይጠቀሙበታል።

የአረብኛ እና አራማይስጥ ስያሜ «አላህ»፣ ዕብራይስጥከነዓንኛ «ኤል፣ ኤሎሂም»፣ አካድኛ «ኢሉ»፣ አማርኛግዕዝም «አምላክ» ምናልባት ከአንድ ምንጭ /*አምላክ/ («አምልኮ የሚገባው») ሊሆን ይችላል። በአውሮፓ ሊቃውንት ዘንድ ግን የቅድመ-ሴማዊ ሥር «*ኢል-» ነበረ።

አላህ እና ጣዖታት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

አንድን እምነት ለማመን ቅድሚያ ስለዚያ እምነት በቂ እውቀት ይጠይቃል፤ በመሃይምነት እውር ድንብር የሆነ ፀለምተኛ እምነት መከልተል በኢስላም አይሰራም፦ 17፥36 ለአንተም በእርሱ #እውቀት #የሌለህን ነገር #አትከተል፤

የእውቀት መጀመሪያ ደግሞ የፈጠረንን ፈጣሪያችንን ማወቅ ነው፤ በኢስላም የመጀመሪያው እርምጃ “ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩ” ማመን ሳይሆን “ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩን” ማወቅ ነው፦ 47:19 እነሆ “ከአላህ ሌላ አምላክ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ አለመኖሩን #እወቅ፤

"ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ"  لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ  "ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ማለት ነው፣ ጣኦታትን የምንክድበት፣  ከአላህ ሌላ በሃቅ ሊመለክ የሚችል አምላክ አለምኖሩን የምናምንበት ቃለ-ምስክርነት ነው፦

2:256 ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ #በጣዖትም "የሚክድ" እና #በአላህ "የሚያምን" ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ 39:17 እነዚያም #ጣዖትን "የሚያመልኳት" يَعْبُدُوهَا ከመሆን የራቁ ወደ #አላህም የዞሩ ለእነርሱ #ብስራት አላቸው፤ ስለዚህ ባሮቼን አብስር ። 43፥26-27 ኢብራሂምም ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ "እኔ ከምታመልኩት ሁሉ #ንጹሕ ነኝ፤ ከዚያ #ከፈጠረኝ #በቀር #አላመልክም እርሱ በእርግጥ ይመራኛልና"። 16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ "#አላህን #አምልኩ #ጣዖትንም #ራቁ" በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤

ይህ ቃለ-ምስክርነት በቁርአን "ጠንካራን ዘለበት" ይባላል፦ 31:22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን وَجْهَهُ ወደ አላህ የሚሰጥም يُسْلِمْ ሰው፣ #ጠንካራ #ገመድ بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፤ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው። 2:256 በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን #ጠንካራ #ዘለበት بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

ይህ ቃለ-ምስክርነት ሁለት ማዕዘናት አለው፤ አንደኛው ነፍይ ሲሆን ሁለተኛ ኢሥባት ነው፤ ይህንን እሳቤ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ "ነፍይ" "ነፍይ" نفي ማለት "አፍራሽ" ሲሆን አሉታዊ ቃል ነው፤ ይህም አሉታዊ ቃል፦ "ላ ኢላሃ" لَا إِلَٰهَ "ሌላ አምላክ የለም" ብለን ስንል ማንኛውንም ጣኦታት ውድቅ የምናደርግበት ነው፤ በቁርአን ከአላህ ውጪ የሚደረግ ባዕድ አምልኮ "ጣኡት" لطَّاغُوتِ ፣ "አውሳን" أَوْثَٰن እና "አስናም" أَصْنَام ይባላሉ፣ እነዚህ ጣኦታት ከዓለማቱ ጌታ ሌላ የሚመለኩ ምንነትና ማንነት ናቸው፤ እጅጉን ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ተለይተው ተቀምጧል፦ 1. "ጣኡት" 2:256 #በጣዖትም لطَّاغُوتِ የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ 4:76 እነዚያ ያመኑት ሰዎች፣ በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፤ እነዛ የካዱትም #በጣዖት لطَّاغُوتِ መንገድ ይጋደላሉ፤ 16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን አምልኩ #ጣዖትንም لطَّاغُوتِ ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤

2."አውሳን" 29:17 ከአላህ ሌላ የምታመልኩት #ጣዖታትን أَوْثَانًا ብቻ ነው፤ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምታመልኩአቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፤ 29:25 ኢብራሂም አለም፦ ከአላህ ሌላ #ጣዖታትን أَوْثَانًا አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው፤ ከዚያም በትንሣኤ ቀን ከፊላችሁ በከፊሉ ይክዳል፤ ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል፤ መኖሪያችሁም እሳት ናት፤ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም።

3. "አስናም" 6:74 ኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር «#ጣዖታትን أَصْنَامًا አማልክት አድርገህ ትይዛለህን እኔ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ. 21:57 በአላህም ስም እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከኼዳችሁ በኋላ #ጣዖቶቻችሁን أَصْنَامًا ተንኮል እሰራባቸዋለሁ፣ አለ። 14:35 ኢብራሂምም ባለ ጊዜ አስታውስ ፦ ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር ጸጥተኛ አድርገው፤ እኔንም ልጆቼንም #ጣዖታትን أَصْنَامًا ከማምለክ አርቀን፤

ነጥብ ሁለት "ኢሥባት" "ኢሥባት" إثبات ማለት "ማፅደቅ" ሲሆን አውንታዊ ቃል ነው፤ ይህም አውንታዊ ቃል፦ "ኢለ ሏህ” إِلَّا اللَّهُ "ከአላህ በቀር" ብለን ስንል አንዱን አምላክ በብቸኝነትና በእውነት ልናመልከው የምናፀድቅበት ነው፤ አንዱ እምላክ አላህ ነገሮችን ካለመኖር ወደመኖር የፈጠረ፣ የሚያሞት ህያው የሚያደርግ፣ መጥቀምና መጉዳት የሚችል፣ ሁሉን የሚያውቅ፣ ሁሉን የሚያይ፣ ሁሉን የሚሰማና በእኔነት የሚናገር ነው፦ 1. "ሁሉን የፈጠረ ነው" 46:4 #ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸው አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ #ፈጠሩ# አሳዩኝ ወይም በሰማያት ለእነርሱ መጋራት አላቸውን? 50:38 ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ #ፈጠርን፡፡ 49:13 እላንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት #ፈጠርናችሁ፤ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፤

2. "የሚያሞት ህያው የሚያደርግ ነው" 30:40 አላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም #የሚያሞታችሁ#፥ ከዚያም #ሕያው# የሚያደርጋችሁ ነው፤ ከምታጋሩዋቸው ጣዖታት ውስጥ ከዚኻችሁ አንዳችን የሚሠራ አልለን? 44:8 ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ #ሕያው ያደርጋል#፣ #ያሞታልም፣ ጌታችሁ፣ የመጀመሪያ አባቶቻችሁም ጌታ ነው።

3. "መጥቀምና መጉዳት የሚችል ነው" 20:89 ወደ እነነሱ ንግግርን የማይመልስ ለእነርሱም #ጉዳትንና #ጥቅምን የማይችል መሆኑን አያዩምን? 10:106 ከአላህም በቀር #የማይጠቅምንና #የማይጎዳን አታምልክ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» ተብያለሁ" በላቸው፡፡ 5:76 ከአላህ ሌላ ለእናንተ #መጉዳትንና #መጥቀምን የማይችልን ታመልካለህን? በላቸው፤

4. "ሁሉን የሚያውቅ ነው" 60:1 #እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን #የማውቅ ስሆን ወደ እነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ፤ 64:4 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፤ የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል አላህ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው።

5. "ሁሉ ተመልካች ነው" 34:11 #እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና። 57፥4 #አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው።

6. "ሁሉን የሚሰማ ነው" 2:186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ #እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ 9:103 ለእነርሱም ጸልይላቸዉ፤ ጸሎትህ ለእነርሱ እርካታ ነዉና አላህም "ሰሚ" ዐዋቂ ነው።

7. "እኔነት ያለው ተናጋሪ ነው" 21:92 "#እኔም" ጌታችሁ #ነኝ እና "አምልኩኝ"። 2:160 እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ #እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ #ነኝ፡፡

ማጠቃለያ ነብያችን"ﷺ" ወደ መካ ሲገቡ በካዕባህ የሚመለኩ 360 ጣዖታትን ሰባብረዋል፤ ያስቀሩት አንድም ጣዖት የለም፤ አል-ሐጀሩል አስወድ ከ 360 ጣዖታት መካከል ነበር የሚለው ዲስኩር የሚሽነሪዎች ቅጥፈት እንጂ የታሪክ ሆነ የሥነ-ቅርስ መረጃ የለም፤ ሐጀሩል አስወድ መጉዳትንና መጥቀምን የማይችልና የአላህን ቤት መዞር የሚጀመርበት መነሻ ነጥብ እንጂ አምልኮ የሚቀበል አይደለም። ይህንን ከሐዲስ መረዳት ይቻላል፦ ኢማም ቡሃሪ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 83: ዑመር ወደ ሃጀሩል አስወድ ቀረቦ ሳመውና፦ አውቃለው #አትጠቅምም #አትጎዳም ነብዩ"ﷺ" ሲስሙህ ባላይ ኖሮ አልስምህም ነበር። عَنْ عُمَرَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُ جَاءَ إِلَى الْحَجَرِ الأَسْوَدِ فَقَبَّلَهُ، فَقَالَ إِنِّي أَعْلَمُ أَنَّكَ حَجَرٌ لاَ تَضُرُّ وَلاَ تَنْفَعُ، وَلَوْلاَ أَنِّي رَأَيْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُكَ مَا قَبَّلْتُكَ‏.‏

ሃጀሩል አስወድ መስማት፣ መናገር፣ ማየት፣ ማወቅ የማይችል ህያው ያልሆነው ነገር ነውና አይጠቅምም አይጎዳም፣ የማይጠቅምና የማይጎዳ ነገር አይመለክም፤ የሚመለከው መጥቀና መጉዳት የሚችለው የሰማያትና የምድር ጌታ ብቻ ነው፦ 13:16 የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው? በላቸው፤ አላህ ነው በል፤ #ለነፍሶቻቸው #ጥቅምንም #ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከእርሱ ሌላ ያዛችሁን? በላቸው፤

የፈጣሪ ሃቅ አምልኮ፣ መለማመን፣ ስለት መሳል፣ መስገድ ወዘተ ነው፤ ይህንን ሃቅ ከመሳም ጋር ማምታታት የለብንም፤ ሲጀመር "መሳም" የመውደድ መገለጫ እንጂ በራሱ መውደድ አይደለም፤ ምክንያቱም ሳንስማቸው የምንወዳቸው ሰዎች ስላሉ፤ ሲቀጥል "መሳም" የፈጣሪ ሃቅ አይደለም፤ ፈጣሪ አይሳምምና፤ ሲሰልስ "መሳም" የፍጡራን መብት ነው፤ አንድ ሰው አባቱን ሳመ ማለት አመለከ ማለት አይደለም፤ አንድ ሰው በእግር ኳስ አሸንፎ ዋንጫ ቢስም አመለከ አይባልም፤ ለሃጅሩል አስወድ አምልኮ፣ መለማመን፣ ስለት መሳል፣ መስገድ ወዘተ ቢቀርብ ኖሮ ይህ ማሻረክ ወይም ባእድ አምልኮ ይሆን ነበር፤ ነገር ግን ይህ ፈፅሞ ሽርክ ነው፤ በኢስላም በድንጋይና በድንጋይ ላይ የሚደረግ አምልኮ "ኑሱብ" نُصُب እና "አዝላም" أَزْلَٰم ሲባል በአላህ ላይ ማሻረክ የሆነ አመፅ ነው፦ 5:90 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፣ ቁማርም፣ "አንሳብ" وَالْأَنْصَابُ "አዝላምም"* بِالْأَزْلَامِ ከሰይጣን ሥራ የሆኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፤ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና። 5:3 ለኑሱብ" النُّصُبِ የታረደው *በአዝላምም* بِالْأَزْلَامِ ዕድልን መፈለጋችሁ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ ይሃችሁ "አመፅ" ነው።

ወሰላሙ አለይኩም

ኢስላም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

Medallion showing "Allah" in Hagia Sophia, Istanbul, Turkey.

በእስልምና እምነት አላህ ማለት ኢላህ ከሚለዉ የአረበኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም አምላክ ማለት ነዉ. ከነብዩ ከአደም (አ.ሰ) ጀምሮ እስከ ነብዩ ሙሃመድ (ሰ.አ.ወ) ድረስ ያሉትን በቁርአን ላይ እንደተጠቀሱት ፪፭ ሃያ አምስት እና ከዛ በላይ ያልተጠቀሱ ነብያትን የላከ አንድ እና ብቸኛ አምላክ. አላህ በቁርአን ላይ የተጠቀሱ ፱፱ (ዘጠና ዘጠኝ) ስሞች አሉት ሁሉም የሚናገሩት ስለማነነቱ እና ስለባህሪዉ ነዉ. የአላህን ማንነት ለማወቅ የፈለገ ሰዉ ስሞችሁን ማስተንተን እና መረዳት ከቻለ አልላህን በመጠኑም ቢሆን ማወቅ ይችላል.

፺፱ (ዘጠና ዘጠኝ) ስሞች አሉት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አር-ረህማን፣ አር-ረሂም፣ አል-መሊክ፣ አል-ቁዱስ፣ አስ-ሰላም፣ አል-ሙእሚን፣ አል-ሙሃይሚን፣ አል-አዚዝ፣ አል-ጀባር፣ አል-ሙተከቢር፣ አል-ኻሊቅ፣ አል-ባሪእ፣ አል-ሙሰዊር፣ አል-ቐፋር፣ አል-ቐሃር፣ አል-ወሃብ፣ አር-ረዛቅ፣ አል-ፈታህ፣ አል-አሊም፣ አል-ቓቢድ፣ አል-ባሲጥ፣ አል-ኻፊድ፣ አል-ራፊእ፣ አል-ሙአዝ፣ አል-ሰሚእ፣ አል-በሲር፣ አል-ሃኪም፣ አል-አዲል፣ አል-ለጢፍ፣