ሀኖይ

ከውክፔዲያ

ሀኖይ (Hà Nội) የቪየትናም ዋና ከተማ ነው።

ሃኖይ የኦፐራ ቤት

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 2,543,700 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,396,500 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 21°01′ ሰሜን ኬክሮስ እና 105°52′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ሃኖይ ዕጅግ ጥንታዊ ከተማ ሆኖ ባታሪክ መዝገብ ብዙ ስሞች ነበሩት። ድሮ ቻይናዎች ቬትናምን ከገዙ በፊት ከተማው ቶንግ ቢኝ ተባለ፤ በኋለኛ ዘመን ደግሞ ሎንግ ዶ ሆነ። በ858 ዓ.ም. ስሙ ዳይ ላ ሆነ። በ1002 ዓ.ም. ዋና ከተማ ሲሆን ስሙ ደግሞ ጣንግ ሎንግ ሆነ። ከ1002 እስከ 1389 ዓ.ም. ድረስ የቬትናም ዋና ከተማ ሲሆን ቆየ። በ1389 ስሙ ደግሞ ዶንግ ዶ ሆነ። በ1400 ዓ.ም. ቻይናዎች ወርረው ያዙትና ስሙን ዶንግ ጯን አሉት። በ1420 ዓ.ም. ወደ ቬትናም ሕዝብ ሲመለስ ስሙ በዚያን ጊዜ ዶንግ ኪኝ ሆነ። ከ1770 እስከ 1794 ዓ.ም. ድረስ ስሙ ባክ ጣኝ ሆነ። በ1794 ዓ.ም. እንደገና ስሙ ጣንግ ሎንግ ሆነ። በመጨረሻም በ1823 ዓ.ም. ስሙ ሃኖይ (ሃ ኖይ) ሆኗል።