Jump to content

ሀይሉ ዲሣሣ

ከውክፔዲያ

ሀይሉ ዲሣሣ ታዋቂ ኢትዮጵያዊኦሮምኛ ድምፃዊ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ እና ተዋናይ ነው።

የህይወት ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሀይሉ ዲሣሣ በ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. በወለጋ ክፍለ ሀገር ልዩ ስሙ ዳሌ ዳርቦ ጃሮ ቱሉ ሰዓ በሚባለው በቄለም አውራጃ በደምቢ ዶሎ ከተማ ተወለደ።

ሀይሉ ዲሣሣ በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም. በሀገር ፍቅር ቲያትር በመቀጠር የኦሮምኛ ግጥምና ዜማን በመድረስ የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ ዜማዎችን ተጫውቷል። ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ድራማዎች ላይ በተዋናይነት ተሳትፏል። በተቀጠረበት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤትም በማገልገል ላይ ይገኛል።

የሥራዎች ዝርዝር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሀይሉ ዲሣሣ ሰባት የተለያዩ የኦሮምኛ ካሴቶችን አሳትሟል።