Jump to content

ሃርፐር ቫሊ ፒ. ቲ. ኤ.

ከውክፔዲያ

ሃርፐር ቫሊ ፒ. ቲ. ኤ.

ርዕስ በሌላ ቋንቋ Harper Valley PTA(እንግሊዝኛ)
የተለቀቀበት ዓመት 1978 እ.ኤ.አ.
ያዘጋጀው ድርጅት
ዳይሬክተር ሪቻርድ ቤኔት
አዘጋጅ ጆርጅ ኤድዋርድዝ
ምክትል ዳይሬክተር
ጸሐፊ ጆርጅ ኤድዋርድዝ፣ ባሪ ሽናይደር
ሙዚቃ ኔልሰን ሪደል
ኤዲተር ማይከል ኤኮኖሙ
ተዋንያን ባርባረ ኢደን፣ ናነት ፋብሬ፣ ሮኒ ኮክስ፣ ሉዊስ ናይ፣ ሱዘን ስዊፍት፣ ፓት ፖልሰን
የፊልሙ ርዝመት 93 ደቂቃ
ሀገር አሜሪካ
ወጭ
ገቢ
ዘውግ {{{ዘውግ}}}
የፊልም ኢንዱስትሪ ሆሊውድ


ሃርፐር ቫሊ ፒ. ቲ. ኤ. (በእንግሊዝኛ: Harper Valley PTA፣ «የሃርፐር ሸለቆ ወላጆችና አስተማሮች ማኅበር») በ1970 ዓም (1978 እ.ኤ.አ.) የተፈጠረ አንድ የአሜሪካ ኮሜዲ ፊልም ነው።

የፊልሙ ታሪክ የተመሠረተው በ1960 ዓም (1968 እ.ኤ.አ.) በተመሳሳይ ስም በወጣው ዘፈን ከጂኒ ራይሊ፣ «ሃርፐር ቫሊ ፒ. ቲ. ኤ. (ዘፈን)» ነበረ። ይሄ በአሜሪካ አገር በነዚህ ዓመታት መካከል የተከሠቱት የባህል ለውጦች በደንብ ይዘግባል።

በታሪኩ ውስጥ፣ ስቴላ ጆንሰን (ተወናይት ባርባረ ኢደን) በሃርፐር ቫሊ ኦሃዮ (ልብ ወለድ መንደር) የምትገኝ ባልዋም ያረፈባት መልከ መልካም ብቸኛ እናት ነች። ለኮስሞቲክ ድርጅት የሰውን በር በማንኳኳት ኮስሞቲክ ትሸጣለች፣ ከዚህም ጭምር በሕይወት ለመደሠት አትፈራም። ሴት ልጅዋ ዲ (Dee) 14 ዓመት ስትሆን የሃርፐር ቫሊ ፪ኛ ደረጃ ተማሪ ነች።

አንድ ቀን ዲ ከትምህርት ቤት ተመልሳ የሃርፐር ቫሊ ወላጆች-አስተማሮች ማኅበር ደብዳቤ ለናትዋ ለስቴላ አመጣች። በደብዳቤውም ዘንድ፣ የስቴላ አለባበስ የመንደሩን ግብረ ገብ ስለማትከብር፣ ለማኅበሩ ደስታ መንገድዋን ካልቀየረች በቅጣት ልጅዋ ከትምህርት ቤቱ ትወገዝ ነበር። የማኅበሩም አለቃ በጣም ጉረኛ ትዕቢተኛ የሆነችው ፍሎራ ሲምሰን-ራይሊ ትባላለች።

በማኅበሩ ግብዝነት ተናድዳ፣ ስቴላ እራስዋ በሚከተለው ማኅበር ስብሰባ ድንገት ገባች። የማኅበር አባላት ምስጢሮችን ገልጣ ግብዞች እንደ ሆኑ በገሃድ አወጣች።

ከዚህ በኋላ አንድ ሌላ ደብዳቤ ከድንጋይ ጋር በስቴላ መኖርያ ቤት በመስኮት ብርጭቆ በኩል ይደርሳል። ከመንደሩ እንድትወጣ ይላል። ከዚህም በኋላ በተረፈው ፊልም ስቴላ በብልሃቶችዋ ቂምዋን አበቀለች፣ የመንደሩንም ኗሪዎች አሳብ ቀየረችና እንኳን እራስዋ የማኅበር አለቃ፣ በመጨረሻም የመንደሩም ከንቲባ ዕጩ ሆነች። አዲስ ባል ደግሞ አግኝታለች።

እንደገና በ1973 ዓም (1981 እ.ኤ.አ.) ባርባረ ኢደን ጋር ሃርፐር ቫሊ ፒ. ቲ. ኤ. (ቴሌቪዥን ትርዒት) ተሠራ።

የውጭ መያያዣ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]