ሃጊያ ሶፊያ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ሃጊያ ሶፊያ

ሃጊያ ሶፊያ በዛሬው ኢስታንቡልቱርክ አገር የሚቆም ዝነኛ ሥነ ሕንጻ ነው።

ህንጻው በ529 ዓም ከተመሠረተ ጀምሮ ቢዛንታይን መንግሥት እስከ ወደቀበት ዓመት እስከ 1445 ዓም ድረስ ጥቅሙ እንደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ካቴድራል ነበረ። ኦቶማን ቱርክ ሃያላት በ1445 ዓም ከያዙበት ወቅት ጀምሮ እስከ 1923 ዓም ድረስ ደግሞ ህንጻው መስጊድ ሆነ። እንደገና በ1927 ዓም ተከፍቶ ከዚያን ጊዜ ወዲኅ ሥፍራው ሙዚየም ሆኖዋል።