ሄራክሌውፖሊስ
Appearance
| ሄራክሌውፖሊስ ኸነን-ነሱት | |
| በሄራክሌውፖሊስ የተገኘ የመቃብር ግድግዳ፣ 2170 ዓክልበ. ግድም | |
ሄራክሌውፖሊስ (ግሪክኛ፦ Ἡρακλεόπολις፤ ግብጽኛ፦ ኸነን-ነሱት) የጥንታዊ ግብፅ ከተማ ነበረ። በመጀመርያው ጨለማ ዘመን የ9ኛውና የ10ኛው ሥርወ መንግሥታት ዋና ከተማ ነበረ። በኋላ በቅብጢኛ ስሙ ህናስ፣ በዱሮ አረብኛ አህናስ፣ በዘመናዊ አረብኛም ኢህናሲያህ ተብሏል። ዛሬ ፍርስራሹ የቱሪስት መድረሻ ሆኗል።
| ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |