Jump to content

ሄስፔሩስ

ከውክፔዲያ

ሄስፔሩስአውሮጳ አፈ ታሪክ ዘንድ የሂስፓኒያ (እስፓንያ) ንጉሥ፣ ከዚያም በኋላ የጣልያን ንጉሥ ነበረ።

አኒዩስአቨንቲኑስና ሌሎች ጸሐፍት እንደሚሉ ሄርኩሌስ ሊቢኩስ በ1929 ዓክልበ. ግድም በእስፓንያ ዓርፎ ሄስፔሩስ ከአለቆቹ አንድ ሲሆን ወዲያው ንጉሥ ሆነ። በኋላ ግን ወንድሙ አትላስ ኪቲም ወይም ኢታሉስ ወደ ጣልያን አባረረው፤ በዚያ መንግሥቱን ከአልቴዩስ ያዘ። «ሄስፔሪያ» የሚባል ስም ለሁለቱ አገራት ለእስፓንያ ወይም ለጣልያን ለማለት ሆነ።

ሄስፔሩስና ወንድሙ አትላስ የያፔቱስ ልጆች ይባላሉ፤ ዲዮዶሮስም እንዲህ ተረከ። ግንኙነት ከማውሬታኒያ አትላንቲክ ጠረፍ ጋር (የአሁኑ ሞሮኮ) እንደ ነበራቸው ይታመን ነበር።

ከጊዜ በኋላ በ1876 ዓክልበ. ግን ወንድሙ አትላስ ኪቲም ከእስፓንያ መጥቶ የጣልያንም መንግሥት ያዘበት፤ ስሙንም «ኢታሉስ» ለሀገሩ (ኢታሊያ፣ ኢጣሊያ) የሰጠው ነው ይጻፋል።

ቀዳሚው
ሄርኩሌስ ሊቢኩስ
የኢስፓኒያ ንጉሥ ተከታይ
አትላስ ኪቲም
ቀዳሚው
አልቴዩስ
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ
1887-1876 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
አትላስ ኪቲም