Jump to content

ኢታሉስ ኪቲም

ከውክፔዲያ
(ከአትላስ ኪቲም የተዛወረ)

ኢታሉስ ወይም አትላስ ኪቲምአውሮጳ አፈ ታሪክ ዘንድ የሂስፓኒያ (እስፓንያ) ንጉሥ፣ ከዚያም በኋላ የጣልያን ንጉሥ ነበረ።

አኒዩስአቨንቲኑስና ሌሎች ጸሐፍት እንደሚሉ ሄርኩሌስ ሊቢኩስ በ1929 ዓክልበ. ግድም በእስፓንያ ዓርፎ ሄስፔሩስ ከአለቆቹ አንድ ሲሆን ወዲያው ንጉሥ ሆነ። በኋላ ግን ወንድሙ አትላስ ኪቲም ወይም ኢታሉስ ወደ ጣልያን አባረረው፤ በዚያም ሄስፔሩስ መንግሥቱን ከአልቴዩስ ያዘ።

ሄስፔሩስና ወንድሙ አትላስ የያፔቱስ ልጆች ይባላሉ፤ ዲዮዶሮስም እንዲህ ተረከ። ግንኙነት ከማውሬታኒያ አትላንቲክ ጠረፍ ጋር (የአሁኑ ሞሮኮ) እንደ ነበራቸው ይታመን ነበር። «ኪቲም» የሚለው ስም ደግሞ ከያዋን ልጆች መካከል ይገኛል።

ከጊዜ በኋላ በ1876 ዓክልበ. ግን አትላስ ኪቲም ልጁን ሲኮሩስ በእስፓንያ ዙፋን ትቶ የጣልያንም መንግሥት ከወንድሙ ያዘበት፤ ስሙንም «ኢታሉስ» ለሀገሩ (ኢታሊያ፣ ኢጣሊያ) የሰጠው ነው ይጻፋል። አንዳንድ መጽሐፍ እንደሚገልጸው፣ መጀመርያ የጋላጤስ ሰዎች በሰፈሩበት በሲኪሊያ ደርሶ ከዚያ አትላስ በመርከቦች እስከ ቲቤር ወንዝ ድረስ ሄዶ ወንዙን ገብቶ ዙሪያውን ያዘ። አትላስ ሴት ልጁን ሮማ በ«አቦሪጌኔስ» (በተራሮችና ከቲቤር ወንዝ ደቡብ የኖሩት ጊጋንቴስ) ወገን ላይ ንግሥት አድርጎ ሾማት። የአትላስ ሌላ ልጅ ሞርጌስ «ኮሪቱስ» ወይም አልጋ ወራሽ አደረገው። የአትላስ ሴት ልጅ ኤሌክትራ የሞርጌስን ተከታይ የአልቴዩስ ልጅ-ልጅ ካምቦብላስኮን አገባችው።


ቀዳሚው
ሄስፔሩስ
የኢስፓኒያ ንጉሥ ተከታይ
ሲኮሩስ
ቀዳሚው
ሄስፔሩስ
ኢታሊያ ንጉሥ
1876-1857 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሞርጌስ