ሄክታር

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ሄክታር የአለም አቀፍ ክልል መለኪያ ሲሆን፣ ትርጉሙ በየጎኑ አንድ መቶ ሜትር ያለው ካሬ (አራት ማዕዘን ያለው) ክልል ስፋት ማለት ነው።

ቃሉ (በፈረንሳይኛ በኩል) የደረሰው ከግሪክኛ ἑκατόν /ሄካቶን/ «መቶ»፣ እና ሮማይስጥ area /አሬያ/ «ክልል» ነበር።

ሄክታር ስለዚህ አሥር ሺህ ካሬ ሜትር አለበት። ሄክታር በተለይ ለመሬት (ርስት ወይም እርሻ) ክልል ለመለካት ይጠቀማል።