Jump to content

ሄፐታይቲስ ኤ

ከውክፔዲያ
ሄፐታይቲስ ኤ
Classification and external resources

A case of jaundice caused by hepatitis A
ICD-10 B15
ICD-9 070.0, 070.1
DiseasesDB 5757
MedlinePlus 000278
eMedicine med/991 መለጠፊያ:EMedicine2
Patient UK ሄፐታይቲስ ኤ
MeSH D006506


ሄፐታይቲስ ኤ (በመደበኛነትተላላፊ ሄፐታይተስ ) በሚል የሚታወቀው አጣዳፊ ተላላፊ በሽታ  የሚያጠቃውም ጉበት ሲሆን ሄፐታይተስ ኤ በሚባል ቫይረስ (HAV)አማካይነት ይተላለፋል። [1] በርከት ባሉ የበሽታው ክስተቶች በተለይም በታዳጊዎች ዘንድ የሚታየው የህመም ምልክት ብዙውን ጊዜ አነስ ያለ ነው ወይም ምንም ምልክት አይታይም። [2] በበሽታው በተያዙ ሰዎች ላይ ምልክቶቹ የሚታዩ ከሆነ ሊታዩ የሚችሉበት ጊዜ በሁለትና ስድስት ሳምንታት መካከል ነው። [3] የህመም ምልክቶቹ ሲኖሩ ለስምንት ሳምንታት ያህል የሚቆዩ ሲሆኑ እነዚህም፦ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ ተቅማጥ፣ የቆዳ ቀለም ብጫ መሆን, ትኩሳት, እና የሆድ ህመምን የሚያካትት ነው። [2] ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በበሽታው ከተያዙበት ጊዜ አንስቶ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተደጋጋሚ የሆነ የህመም ምልክቶቹን ያያሉ። [2] አጣዳፊ የጉበት ስራ ማቆም ችግር አልፎ አልፎ ሲከሰት በአረጋዊያን ዘንድ ግን ክስተቱ የተለመደ ነው። [2]

ብዙውን ጊዜ በሽታው የሚሰራጨው ቫይረሱ ባለበት አይነምድር የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ በመብላትና በመጠጣት ነው። [2]  [[ሼልፊሽ/የባህር ዓሳ]ን በደንብ ሳይበስል ከተመገቡት እሱም አንዱ የበሽታው ምንጭ ነው። [4] እንዲሁም በበሽታው በተያዘ ሰው ጋር በሚኖር የቅርብ ግንኙነት/ንኪኪ ሊተላለፍ ይችላል። [2] ምንም የህመም ምልክት የማይታይባቸው ህፃናትም ቢሆኑ በሽታውን ወደ ሌሎች ማስተላለፍ ይችላሉ። [2] አንድ ሰው አንዴ በበሽታው ተይዞ ከዳነ ዕድሜ ልኩን ተመልሶ አይያዝም /እንደ ክትባት ያገለግለዋል። [5] የህመም ምልክቱ ከሌሎች በርካታ በሽታዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ በሽታውን ለማወቅ በሚደረግ ምርመራ የደም ናሙና ወስዶ ማየት ያስፈልጋል። [2] ይህ ከሚታወቁት አምስት ሄፐታይቲስ ቫይረስ: ኤ, , and  መካከል አንዱ ነው።

የ ሄፐታይቲስ ኤ ክትባት  በሽታውን ለመከላከል ውጤታማ ነው። [2][6] አንዳንድ አገሮች ለህፃናት በተከታታይ ሲሰጡ በህፃንነታቸው ላልተከተቡና በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ሆኖ ለተገኘ አዋቂዎችም ክትባቱ እንዲሰጣቸው ያደርጋሉ። [2][7] ክትባቱ ለዕድሜ ልክ ያገለግላል። [2] ሌሎች የመከላከያ ዘዴዎች [እጅን መታጠብ]] እና ምግብ በደንብ ማብሰልን ያጠቃልላል። [2] ምንም የተለየ ህክምናም የለውም፤ ለ ማቅለሽለሽ ወይም ተቅማጥ እረፍትና መድሃኒት እንዳስፈላጊነቱ ሊታዘዝ ይችላል። [2] በሽታው ብዙውን ጊዜ ያለ ቀጣይ የጉበት ህመም ሙሉ በሙሉ ይድናል። [2] አጣዳፊ የጉበት ስራ ማቆም ችግር ከተከሰተ፤ ህክምናው ጉበት የመቀየርዘዴን መጠቀም ያስፈልጋል። [2]

በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከሚታይባቸው ምልክቶች በመነሳት ምርመራ ሲደረግላቸው በሽታው የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ይሆናል። [2] ባጠቃላይ አስር ሚሊዮኖች ይያዛሉ ተብሎ ይገመታል። [8] የበሽታው ክስተት በብዛት የሚታወቀው ዝቅተኛ የግልና የአካባቢ ንጽና ባለበትና በቂ ንፁህ ውሃ በሌለው የዓለም ክፍል ነው። [7] በበማደግ ላይ ባለው ዓለም 90 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት በ10 ዓመት ዕድሜያቸው በበሽታው ስለሚያዙ አዋቂዎች በሚሆኑበት ጊዜ መልሰው አይያዙም። [7] ህፃናት በልጅነታቸው ጊዜ ለበሽታው ባማይጋለጡባቸው ባደጉት አገሮች ለአዋቂዎች በቂ ክትባት በማይኖርበት ወቅት በሽታው በወረርሽኝ መልክ ይከሰታል። [7] በ 2010, አጣዳፊ የሄፐታይቲስ ኤ በሽታ 102,000 ሰዎችን ለህልፈት ደርጓል። [9] የዓለም ሄፐታይቲስ ቀን  በየዓመቱ ጁላይ 28 ስለ ቫይራል ሄፐታይቲስግንዛቤ ለመፍጠር ይከበራል። [7]

  1. ^ . 
  2. ^ Matheny, SC; Kingery , JE (1 December 2012). "Hepatitis A.". Am Fam Physician  86 (11): 1027–34; quiz 1010–2. PMID 23198670 . http://www.aafp.org/afp/2012/1201/p1027.html. 
  3. ^ . 
  4. ^ . March 2013 . 
  5. ^ The Encyclopedia of Hepatitis and Other Liver Diseases. Infobase . 2006. p. 105. ISBN 9780816069903. http://books.google.ca/books?id=HfPU99jIfboC&pg=PA105. 
  6. ^ . 
  7. ^ "Hepatitis A Fact sheet N°328". World Health Organization (July 2013). በ20 February 2014 የተወሰደ.
  8. ^ Wasley, A; Fiore, A ; Bell, BP  (2006). "Hepatitis A in the era of vaccination.". Epidemiol Rev  28: 101–11. doi:10.1093/epirev/mxj012 . PMID 16775039 . http://epirev.oxfordjournals.org/content/28/1/101.long. 
  9. ^ Lozano, R (Dec 15, 2012). "Global and regional mortality from 235 causes of death for 20 age groups in 1990 and 2010: a systematic analysis for the Global Burden of Disease Study 2010". Lancet 380 (9859): 2095–128. doi:10.1016/S0140-6736(12)61728-0. PMID 23245604.