ሆተፒብሬ

ከውክፔዲያ
ሆተፒብሬ
በኤብላ የተገኘው የሆተፒብሬ ዱላ
ኤብላ የተገኘው የሆተፒብሬ ዱላ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1806-1803 ዓክልበ.
ቀዳሚ አመኒ ቀማው
ተከታይ ዩፍኒ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት አመኒ ቀማው?


ሆተፒብሬ ቀማው ሲሃርነጅሀሪተፍ (ወይም ሰሀተፒብሬ) ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1806 እስከ 1803 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የአመኒ ቀማው ተከታይ ነበረ። ሕልውና ከአንዳንድ ቅርስ ተረጋግጧል። ከነዚህ በተለይ የሚጠቀሰው በኤብላ የተገኘ ዱላ ቅርስ ነው፤ ይህ በኤብላ ገዥ ኢመያ መቃብር በመገኘቱ የሆተፒብሬም ስም ስላለበት ከፈርዖኑ ለኢመያ የተሰጠ ስጦታ እንደ ነበር ይገመታል።

የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት እንደሚያስረዳው የአመኒ ቀማው ልጅና ተከታይ ይሆናል። ስያሜው «ቀማው ሲሀርነጅሀሪተፍ» ማለት «የቀማው ልጅ ሲሀርነጅሀሪተፍ» ይመስለዋል።

በራይሆልት አስተሳሰብ፣ የሆተፒብሬ ተከታይ ዩፍኒ ሲሆን ይህ ምናልባት ወንድሙ ወይም አጎቱ ይሆናል።

ቀዳሚው
አመኒ ቀማው
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1806-1803 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ዩፍኒ

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)