Jump to content

ለካዉ

ከውክፔዲያ

ግእዝ ቋንቋ እንማር፦

  • ሰላም ለኩልክሙ = ሰላም ለእናንተ ይሁን
  • እፎ ሀለውክሙ = እንዴት አላችሁ
  • ለእመ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ = ግእዝ ቋንቋ ብንማር
  • ምንት ይመስለክምሙ? = ምን ይመስላችኋል

የግእዝ ቋንቋ አስፈላጊነት እና አሁን ያለበት ሁኔታ፦

ግእዝ ቋንቋ በኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ እስከ አጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ-መንግሥት ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ነበር።

በግእዝ ቋንቋ የኢትዮጵያ ታሪክ፥ የቤተክርስቲያን መጻሕፍት ከግሪክ፥ ከዕብራይስጥ፥ ከአረብኛ፥ ከሱርስት ቋንቋዎች የተተረጎሙብት ጥንታዊ ቋንቋ ነው። ላቲን የምዕራባውያን ቋንቋ እና ታሪክ መሠረት እንደሆነ ግእዝም የኢትዮጵያውያን ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ወግ፥ ልማድ፥ ሃይማኖት፥ ጥበብ፥ ፍልስፍና መሠረት ነው።

ኢትዮጵያን ለማጥናንት፥ የአባቶችን ጥበብ ወደ ልጆች ለማስተላለፍ ግእዝ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ግእዝ አሁን በኢትዮጵያ በመጠኑም ቢሆን በአሁኑ ሰዐት አገልግሎት የሚሰጠው በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው። በአሁኑ ሰዓት የግዝ መጻሕፍት ሁሉ ወደ አማርኛ በመተርጎም ላይ በመሆናቸው፣ የቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎትም ሕዝቡ ወደሚጠቀምበት ቋንቋ ወደ አማርኛ እያደላ ይገኛል። አግልግሎቱ በማኅሌትና፥ ከዜማ ጋር በተያያዙ አገልግሎቶች እየተወሰነ ነው።

በሀገር ደረጃም፥ እንኳን ኢትዮጵያውያንን መላውን አፍሪካ የሚያኮራው ብቸኛው የአፍሪካውያን የግእዝ ፊደል እና የግእዝ ቋንቋ በወቅቱ ባለው አገርና ታሪክን የሚገድል የክፍፍክ ፖለቲካ ሂደት ምክንያት ተገቢው ትኩረት ተነፍጎታል፤ አንዲያውም የነጻነት ቤቱን፥ ተወልዶ ያደገበት ሀገሩን ኢትዮጵያንም እንዲለቅ የላቲኖች ፊደል ቅኝ ግዦቹ ሆነው ገብተው በገዛ-ምድሩ ላይ ነጻነቱን፥ ታላቅንቱን፣ መብቱን ገፈውት ይገኛል። በግዝ ፊደል በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋዎችን ሁሉ መጻፍ እንደሚቻል፣ ከዚያም አልፎ ለእናቱ ፍሪካም «አንድ ለናቱ» እንደ ሆነ ይታወቃል። እንኳ ኢትዮጵያውያን የላቲንን ፊደል እደ ጣሊያን ወታደር መርዝ አስታጥቀው ወደ ኢትዮጵያ የላኩት ምዕራባውያንም አሳምረው ያው ቃሉ። ግእዝና የግእዝንም ፊደል እናስታምምህአለን ብለው በቤታቸው (በአውሮጳ) እስተኝተው ሞቱንም ሽረቱንም እየተከታተሉት ነው። ይህም ማለት በጉለበት እየቀሙ የወሰዱአቸው ግእዝ መጻሕፍት በብዛት በእጃቸው ይገኛሉ፣ በልዩ ልዩ ትምህርት ቤቶችም ግእዝ ቋንቋን ያስተምራሉ። ይህም የግእዝን ማንነት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያንን ክብርና ጥበብ እንዲረዱ ማገዙ የታወቀ ነው። ታዲያ ያን እያወቁ ለምን በኦሮምያ ክልል የግእዝ መልክ እንዲጠፋ ወሰኑበት?

የሚሳዝኑት የፍሪካን ማንነት መገለጫ የሁኑትን ታሪኮች፥ ቋንቋዎች፥ ፊደሎች ሁሉ እንዳጠፉ በታሪክ የሚታዎቁትና የላቲንን ፊደልን በግእዝ ፊደል ለመተካት የወሰኑት ምዕራባውያን አይደሉም፣ የሚያስገርሙት በቀደመው የባርንት ዘመን አፍሪካውያን የገዛ ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ከባርያ ፈንጋዮች ተዋግተው በማትረፍ ፈንታ ተባባሪወች በመሆናቸው፥ በታሪክም፦ በትውልድም ላይ የፊት ሀፍረት የሆነ በደል ሰርተው እንዳለፉ ሰዎች፥ አሁንም በሀገራችንም የግእዝን ፊደል፥ በላቲን ተክተው፥ ለመጠቀም የተስማሙ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የአፍሪካውያን ሁሉ የነጻነትን እና ማንነት ምልክት የሆነውን፣ ልጆቻቸው የኛ የሚሉትን እና መለያ ምልክታቸው የሆነውን የግዝ ፊደል ቦታ፥ ለላቲን ፊደል በመስጠታቸው አሰነዋሪ ታሪክ የሆንባቸዋል፤ አሁን ቀኝ ገዞች በተወገዱበት፣ የባሪያ አሳዳሪው ስርአትም በተንኮታኮተበት ዘመን፣ አፍሪቃዊው ግእዝ በላቲን ፊደል ሀገሩን ለምን ይቀማል? ለምንስ ሌሎች ነጻነቱን በሀገሩ ላይ ገፈውና ማርከው፥ በላዩ ላይ ሌላ የላቲን ፊደል ሹመው፥ ወደ አሮፓ ወሰዱት? የኢትዮጵያውያንን የክብር ፊደል፥ የፍሪካን ምልክት ማነው በሀገሩ ላይ በላቲን ሰንሰለት እጅ እግሩን ያሰረው?

ተፈቶ በነጻነት ሊሄድ ይገባዋል፤ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የራሳችውን ፊደል ሊጠቀሙ እንጂ፥ «የሰው ወርቅ አያደምቅ» እንዲሉ የሚታወቁት በጥንታዊ ግእዝ ፊደላችው እና ቋንቋቸው ስለሆነ የግእዝን ቋንቋ ማወቅና ማሳወቅ፥ ወደ ትውልድም ማስተላለፍ፥ የሁሉም ኢትጵያውያን ኃላፊነት ነው። የግእዝን ቋንቋ ወደ ትውልድ ማስተላለፍ ማለት ታሪክን፣ ክብርን፣ ማንነትን፣ ሃይማኖትን፣ ጥበብን፣ አብነትን ለትውልድ ማቆየትና ራስንም ማወቅ ነው።

ግእዝ እንማር

ግእዝ ቋንቋ በቀለሉ ሊጠና የሚችል፥ የተስተከከለ የቋንቋ ህግ ያለው፥ ጥንታዊ ቋንቋ ነዉ፤ ስለዚህ ይህን ጥንታዊ ቋንቋ መማውርና የኢትዮጵያን ጥንታውያን መጻሕፍት መመርመር ለምትፈልጉ ሁሉ የቋንቋውን በር የሚከፍት ትምህርት ለመስጠት ዝግጁ አስተማሮች አይነተኛ ናቸው።