ሉዊ ፓስቴ

ከውክፔዲያ
ሉዊ ፓስቴ

ሉዊ ፓስቴ (Louis Pasteur) (1815 – 1888 ዓ.ም.) ፈረንሳያዊ የረቂቅ ህዋሳትና የኬሚስትሪ ሊቅ ነበሩ። እሳቸውና ሚስታቸው ማሪ ፓስቴ በተለይ በበሽታዎች ጀርም ቲዎሪ ስላደረጉት ሙከራዎች ይታወቃሉ። እንዲሁም በክትባት ስለ መስራታቸው ይታወቃል። በተለይም በውሻ በሽታ የሚከላከል መጀመርያው ክትባት በማግኘቱ ስመ ጥሩ ናቸው። በኬሚስትሪ በኩል የቡረሌ ኢምጥጥናዊ አቀራረጽ አሳወቁ። ከዚህም በላይ ወተትወይን ጠጅ ቶሎ እንዳይበላሽ ዘዴ አገኙ። ይህም ሂደት ፕስተራ (pasteurization) ይባላል።