ሌፍኮዚያ
Appearance
ሌፍኮዚያ (Λευκωσία, Lefkoşa) የቆጵሮስ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 197,600 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 35°09′ ሰሜን ኬክሮስ እና 33°21′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ሌፍኮዚያ በጥንት ሌድራ የተባለ ከተማ-አገር ነበር። የሌድራ ንጉስ ኦናሳጎራስ ለአሦር ንጉስ አስራዶን በ680 ክ.በ. ቀረጥ እንደ ገበሩ ይመዘገባል። 300 ክ.በ. ገዳማ በግብጽ ንጉሥ 1 ፕቶሎማዮስ ልጅ በሌኮስ አዲስ ተሰርቶ ስሙ ደግሞ ሌፍኮጤያ ሆነ። በግሪክና ሮማውያን ዘመኖች ትልቅ መንደር አልነበረም። በ340 ዓ.ም. መጀመርያ ኤጲስ ቆፖሱን ትሪፊሊዮስን ባገኘው ጊዜ ስሙ ሌድሪ ወይም ሌፍኩሲያ ተባለ።
በወደቦቹ ላይ አደጋ በአረቦች ስለ ተጣለ ሰዎችም ወደ ሌፍኮዚያ ስለ ሸሹ ከተማው በትልቅነት አደገና በ10ኛ ክፍለ ዘመን ገዳማ የደሴቱ ዋና ከተማ ሆነ። በ1184 ዓ.ም. ፈረንጆች (የመስቀል ጦርነት ሠራዊት) ያዙትና ስሙን ኒኮሲያ አሉት። ስለዚህ እስከ ዛሬ ድረስ በምዕራባውያን አገራት ቦታው 'ኒኮሲያ' ይባላል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |