ሐሳባዊነት

ከውክፔዲያ

ሐሳባዊነት ሊታዎቅ የሚችለው ዓለም (በሌላ አባባል የውኑ ዓለም ) ሥረ መሠረት ወይም አዕምሮ ወይም ደግሞ መንፈስ ነው የሚል ነው። ከቁስ አካልዊነት በትይይዩ ያለ የፍልስፍና ክፍል ነው። ኅሊና ከቁስ አካላት በላይና ቀዳሚ ነው የሚልን አስተሳሰብ ያራምዳል። በዚህ ግዙፍ የፍልስፍና ጥላ ስር የሚንሸራሸሩ ብዙ ዓይነት ፍልስፍናዎች አሉ። ከብዙ በጥቂቱ፦

  1. ኅሊናዊ ሐሳባዊነትሐሳባችን እና አዕምሯችን ብቻ በእርግጠኝነት እንዳሉ (ኅልው እንደሆኑ) ሊታዎቅ ይቻላል። ከዚህ ውጭ ያለው ማናቸውም ነገር በእርግጠኝነት መታዎቅ ስለማይችል፣ ፋይዳ የለሽ ነው ይላል። የማናቸውም ነገር ኅልውና መሰረት በአዕምሮ ውስጥ መታሰቡ ብቻ ነው።
  2. ምጥቃዊ ሐሳባዊነትነገሮች-በራሳቸውን ማዎቅ አንችልም። ይልቁን ለኛ የሚመስሉንን ያክል ነገሮችን እናውቃቸዋለን የሚል ነው። ለምሳሌ አበቦች ለንቦች የተለየ መልክ አላቸው። ይሁንና ሰዎች አበቦችን፣ ለሰዎች በሚመስሉት ልክ እንደሚረዱ ማለት ነው።
  3. መንፈሳዊ ሐሳባዊነት፡ ሌላ ከፍተኛና ግዙፍ አዕምሮ ወይንም መንፈስ ከኛ አዕምሮ ጋር ሲገናኝ የሚፈጥረው ዓለም ፣ የውኑና ሊታዎቅ የሚችለው ዓለም ነው።
  4. ፍጹም ሐሳባዊነት፡ የሰው አዕምሮ ዓለምን ለመረዳት እንዲችል ቢያንስ በአንድ አይነት ህኔታ ሐሳብ እና ኑባሬ አንድነት አላቸው የሚል ነው።

ሆነም ቀረ፣ ሐሳባዊነት ከሁሉ አስቀድሞ ሐሳብን የሁሉ ነገር መሰረት በማድረጉ ይታዎቃል።