መሃመድ አማን
Appearance
መሐመድ አማን በመካከለኛ ርቀት በተለይ በ፰ መቶ ሜትር የሩጫ ውድድር የሚሳተፍ ኢትዮጵያዊ ነው። በሐገራችን አቆጣጠር ጥር ፪ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም በአሰላ ከተማ የተወለደው መሃመድ እ.ኤ.አ በ2009 እና 2011 የአፍሪካ ታዳጊ አትሌቶች ውድድሮች ላይ በ800 ሜትር አሸናፊ መሆን ችሎ ነበር።
በለንደን ኦሎምፒክስ ተሳትፎ የነበረው መሃመድ ሁለት ዙር ማጣሪያዎችን አልፎ ለፍጻሜ ውድድር በማለፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አትሌት ለመሆን በቅቷል። በፍጻሜው ውድድር ሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ባይችልም የራሱን እና የኢትዮጵያን ክብረ-ወሰን በማሻሻል ነበር ውድድሩን ያጠናቀቀው። ከኦሎምፒክስ በኋላ በተከፈተው የዳይመንድ ሊግ ውድድር የተሳተፈው መሃመድ በዙሪክ በተካሄደ የ800ሜትር ውድድር ላይ የዓለም ሪከርድ ባለቤቱን ኬንያዊ ዴቪድ ሩሺዳን ቀድሞ በመግባት አሸናፊ ሆኗል። በዚህም ውድድር የራሱን እና የኢትዮጵያን ሪከርድ በማሻሻል ነው ያጠናቀቀው። [1]
- ^ "ሞሃመድ አማን በስዊዘርላንድ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸነፈ". thearadaonline.com (31 Aug 2012). Archived from the original on 28 September 2012. በ31 Aug 2012 የተወሰደ.