Jump to content

መለጠፊያ:የፖለቲካ ምርጥ ጽሑፍ

ከውክፔዲያ

ዴሞክራሲ


ዴሞክራሲፖለቲካ ሥርዓት ሲሆን ትርጓሜውም ሕዝባዊ መንግስት ማለት ነው። በሌላ አባባል ዲሞክራሲ ማለት ህዝብ የሚያስተዳድረውን አካል ያለምንም ተፅዕኖ ከመካከሉ መርጦ ሥልጣን የሚሰጥበት ሥርዓት ነው።

የዲሞክራሲ መጠን በያገሩ (2009 ዓ.ም. )
*ሰማያዊ -- በጣም ዲሞክራሲያዊ (ዎደ 10 የተጠጋ
*ጥቁር -- ትንሽ ዲሞክራሲያዊ (ዎደ 0 የተጠጋ)
  • ዴሞክራሲ ለምን ተፈለገ?

እንደ ፈላስፋው ጆን ስቱዋርት ሚል ሦስት ምክንያቶች ይጠቀሳሉ፦

ሕግ አርቃቂዎች ለአንድ ሕብረተሰብ ጥቅም፣ መብት እና አስተሳሰብ ትኩረት እንዲሰጡ ከሌሎች የፖለቲካ ሥር ዓቶች በላይ ዴሞክራሲ ያስገድዳቸዋል። ስለዚህ ሰዎች በሥርዓቱ ውስጥ የመጎዳታቸው ዕድል አንስተኛ ነው። ተመራማሪ ዓማርትያ ሴን ዋቢ ሲሰጥ «በ[ታሪክ ውስጥ ] በማናቸውም ሉዓላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስታት ከፍተኛ ርሃብ ተከስቶ አያቅም» ይላል። ፖሊሲ አውጭዎች ለሕዝብ ተገዥ ስለሆኑ።

ዴሞክራሲ አብዛኛውን ሕዝብ በውሳኔ አስጣጥ ላይ ስለሚያካፍል፣ ከሌሎች የፓለቲካ ሥርዓቶች በበለጠ የዜጎችን ጉዳይ ያዎቀ ሆኖ ይገኛል። በውሳኔ አሰጣጥ የሚካፈለው ሕዝብ መብዛት በሌላ ጎን ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እሚደረገውን ስራ ያግዛል፣ ተሳታፊዎችም ስለ ጉዳዮች የበለጠ የተተቸና የተብራራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይረዳል።

    • የዜጎችን ባሕርይ የማሻሻል ምክንያት

በዴሞክራሲ ሥርዓት ያሉ ሰዎች በውሳኔዎች ላይ ስለሚሳተፉ፤ ከሌሎች ሥርዓት ሰዎች በተለየ እራሳቸውን ችለው እንዲያስቡ፣ በሃሳባቸው ምክኑያዊ እንዲሆኑ እና የሌሎችን መብቶች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ስለሚገደዱ በሥነ ምግባር እንዲሻሻሉ ይሆናሉ።

ዴሞክራሲ ከሚያስከትለው ጥቅም ውጭ በጥቅመኝነት የማይገኙ ሌሎች ሥነ ምግባራዊ ምክንያቶችይጠቀሳሉ። ለምሳሌ ሓርነትዕኩልነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የመናገር መብት፣ ፍትህ ይጠቀሳሉ