መለጠፊያ:ይህን ያውቃሉ

ከውክፔዲያ

- በዓለም ላይ በግዙፍነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ትልቁ መፅሐፍ 31ሺ ኪሎ ግ ራም 310 ኩንታል ክብደት ያለው ሲሆን መፅሐፉን ለመጠረዝ የ34 ሺ ፍየሎች ቆዳ ፈጅቷል፡፡ ይህንን መፅሐፍ አንብቦ ለመጨረስ ብቻ 6 ዓመት ይፈጃል፡፡

- በዓለም ላይ በግዙፍነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ትልቁ መፅሀፍ ቅዱስ የሎስአንጀለስ አናፂ ለሁለት ዓመታት ቀንና ሌሊት ከእንጨት ሰርቶ ያዘጋጀው መፅሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ የዚህ መፅሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ገፅ ከ3 ጫማ በላይ ርዝመትና 8.048 ጫማ ውፍረት አለው፡፡

- በዓለም ላይ በትንሽነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ትንሹ መፅሐፍ ቅዱስ በእንግሊዝ ሃገር የታተመው ሲሆን መጠኑም የአንድ ክብሪት ሳጥን ያህላል፡፡ በውስጡም 878 ገፆችና በርካታ ስዕሎች አሉት፡፡ ይህ መፅሐፍ ቅዱስ የሚነበበው በአጉሊ መነፅር ብቻ ነው፡፡

- በዓለም ላይ ከሚገኙት ጎሳዎች ሁሉ በቁመታቸው ረጃጅም የሚባሉ ጎሳዎች በማዕከላዊ አፍሪካ ክልል በሩዋንዳና ቡሩንዲ የሚኖሩት የቱትሲ ጎሳዎች ናቸው፡፡ የቁመታቸው አማካይ ርዝመትም 1 ሜትር ከ83 ሳንቲ ሜትር ነው፡፡

- በዓለም ላይ ከሚገኙት ጎሳዎች ሁሉ በቁመታቸው አጫጭር የሚባሉት ጎሳዎች በቀድሞዋ ዛየር በአሁኗ ዲሞክ ራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚኖሩት የፒግሚ ጎሳዎች ናቸው፡፡ የቁመታቸው አማካይ ርዝመትም የወንዱ 1 ሜትር ከ37 ሳ.ሜ ሲሆን የሴቷ ደግሞ 1 ሜትር ከ24 ሳ.ሜ ነው፡፡

- በዓለም ላይ እስከ አሁን ከተሰሩት ፊልሞች ውስጥ በጣም በርካታ እንስሳት የተሳተፉበት ብቸኛው ፊልም #Around the World in 80 days$ የተባለው ፊልም ሲሆን በዚህ ፊልም ላይ 4 ሰጎኖች፣ 15 ዝሆኖች፣ 17 በሬዎች፣ 512 ዝንጀሮዎች፣ 800 ፈረሶች፣ 950 አህዮች እና 2448 ጎሾች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

- በዓለም ላይ ካሉት ሴቶች መካከል በህፃንነቷ አርግዛ በመውለዳ ስሟ ለዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ የተመዘገበችው ሴት የፔሩ ዜጋ የሆነችው ሊና ሜዲና ትባላለች፡፡ ሊና ሜዲና አርግዛ የወለደችው የ5 ዓመት ልጅ ሳለች ነው፡፡ ሊና የ10 ዓመት ልጅ ሳለች ልጇ ደግሞ የ5 ዓመት ልጅ ስለነበረች እናትና ልጅ የተማሩት አብረው በአንድ ክፍል ውስጥ ነው፡፡

- የመጀመሪያዋ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው አውሮፕላን ፓቴዝ ትባላለች::የመጣችውም ከፈረንሳይ በ1922 ሲሆን የዚች አውሮፕላን ገጣጣሚዋ አንድሬ ሜሬዝ የተባለ ፈረንሳዊ ነው::

- የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያ ውስጥ የተገጣጠመችው አውሮፕላን "ጸሃይ" ስትባል ይህን ስያሜ ያገኘችውም በአጼ ሃይለ ስላሴ ሴት ልጅ በልእልት ጸሃይ ሃ/ስላሴ ስም ነበር:: ነገር ግን ይህችን አውሮፕላን የገጣጠማት ጀርመናዊ አውሮፕላኗን ኢትዮጵያ አንድ በማለት ነበር የሰየሟት::

- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ቴአትር ቤት የሃገር ፍቅር ቴአትር ሲሆን የተመሰረተው በ1927 የሃገር ፍቅር ማህበር በሚል ስም ነበር::

- ለመጀመሪያ ግዜ በሚኒልክ መልክ ታትመው የወጡት ገንዘቦች ስራ ላይ የዋሉት በ1886 አ.ም ነበር::

- የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዶክተር /ዶክተር ማርቲን/ እየተባሉ የሚጠሩት ሃኪም ወርቅነህ እሸቴ ነበሩ::

- የመጀመሪያው የሃገራችን ሆስፒታል ስራውን የጀመረው መጋቢት 7 ቀን በ1890 አ.ም ሲሆን የሆስፒታሉም ስም ዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል ይባላል::