መርሰኸምሬ

ከውክፔዲያ
መርሰኸምሬ
«መርሰኸምሬ ነፈርሆተፕ» የሚል አንዱ ሐውልት
«መርሰኸምሬ ነፈርሆተፕ» የሚል አንዱ ሐውልት
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1656-1653 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሰዋጅተው
ተከታይ ሰውጅካሬ ሆሪ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት


መርሰኸምሬላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1656 እስከ 1653 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ መርሰኸምሬ የታወቀው ከሦስት ምንጮች ነው፦

  1. ቶሪኖ ቀኖና ሰነድ፣ ከሰዋጅተው ቀጥሎ «መርሰኸምሬ ኢነድ» ተዘረዘረ። ሦስት አመት፣ አንድ ወርና አንድ ቀን እንደ ነገሠ ይላል።
  2. ካርናክ ዝርዝርም ላይ አንድ «መርሰኸምሬ» ይገኛል፣ ይህ ዝርዝር ግን ቅድመ-ተከተል አይጠብቅም።
  3. ሁለት «መርሰኸምሬ ነፈርሆተፕ» የሚሉ ሐውልቶች በሥነ ቅርስ ከካርናክ ተገኝተዋል።

ብዙ ሊቃውንት እንደሚሉ፣ ሁላቸው አንድ ነውና የመርሰኸምሬ ሌሎች ስሞች ኢነድነፈርሆተፕ ናቸው። አንዳንድ መምህር ግን «መርሰኸምሬ ኢነድ»ና «መርሰኸምሬ ነፈርሆተፕ» ልዩ ልዩ ፈርዖኖች ነበሩ ብለው ያምናሉ።

በዚሁ ዘመን የሥርወ መንግሥቱ ሥልጣን ከጤቤስ ከተማ በጣም እንዳልራቀ፣ ሂክሶስም ወገኖች በስሜን እንደ ገዙ ይታስባል።

ሌላው «መርሰኸምሬ ነፈርሆተፕ» የሚለው ሐውልት
ቀዳሚው
ሰዋጅተው
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1656-1653 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰውጅካሬ ሆሪ

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)