መንቱሆተፒ
Appearance
==
| ሳንኸንሬ መንቱሆተፒ | |
|---|---|
| «ሳንኸንሬ» የሚል እስፊንክስ ቅርስ | |
| የግብጽ ፈርዖን | |
| ግዛት | 1636-35 ዓክልበ. ግ. |
| ቀዳሚ | 3 ነፈርሆተፕ |
| ተከታይ | 1 ነቢሪራው |
| ሥርወ-መንግሥት | 16ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ሳንኸንሬ መንቱሆተፒ (ወይም «7 መንቱሆተፕ») በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1636-1635 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
ስሙ «ሳንኸንሬ መንቱሆተፒ» የሚታወቀው ከአንዳንድ ቅርስ ነው።
- በካርናክ የተገኘ ጽላት «የጤቤስ ንጉስ» እንደ ተባለ ከሂክሶስም ጋር እንደ ተዋጋ ይገልጻል።
- «ሳንኸንሬ» በሚል በአንድ ጥንዚዛ ቅርጽ
- ሁለት እስፊንክስ ምስሎች በኤድፉ በ1916 ዓም ተገኙ፣ አንዱ «ሳንኸንሬ» ሲል ሌላው «መንቱሆተፒ» ይላል።
- በቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ «ሰ...ኧንሬ» ለ1 ዓመት እንደ ገዛ ይላል። ሙሉ ስም አሁን ሊነብብ አይቻልም።
| ቀዳሚው 3 ነፈርሆተፕ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1636-1635 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 1 ነቢሪራው |