1 ነቢሪራው

ከውክፔዲያ
ሰዋጀንሬ ነቢሪራው
«ሰዋጀንሬ» የሚል ጩቤ
«ሰዋጀንሬ» የሚል ጩቤ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1635-14 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ መንቱሆተፒ
ተከታይ 2 ነቢሪራው
ሥርወ-መንግሥት 16ኛው ሥርወ መንግሥት


ሰዋጀንሬ ነቢሪራውላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1635-1614 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ «ሰዋጀንሬ ነቢሪራው» የሚታወቀው ከአንዳንድ ቅርስ ነው።

  • በአንድ ጽላት ላይ («የካይሮ ፍትሓዊ ጽላት») ከፈርዖን ነቢሪራው 1ኛ ዓመት (1635 ዓክልበ.) ሲሆን አያመሩ የተባለ መኮንን የኤል-ካብ አገረ ገዥ በመርሆተፕሬ ኢኒ 1ኛ አመት (1661 ዓክልበ.) እንደ ተሾመ ይጠቅሳል።
  • አንዳንድ ማህተም ወይም ጥንዚዛ ምልክት፣
  • «ሰዋጀንሬ» በሚል መዳብ ጩቤ።
  • ቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ «ነቢሪ-አውትሬ» ወይም ነቢሪራው ለሃያ-(?) አመት እንደ ገዛ ይላል። በአንዳንድ መምህር ዘንድ 29፣ 27, ወይም 26 አመት ነበር፣ ሁለተኛው ቁጥር በደንብ አይነበብም። ከርሱ ቀጥሎ ሁለተኛው ነቢሪራው ወይም «ነቢታውሬ» ይጠቀሳል።

በተጨማሪ ከዚያ 1500 ዓመት በኋላ በ150 ዓክልበ. ያህል የተሠራ አንድ ጣኦት ምስል ይታወቃል፤ በመሠረቱ በየጎኑ «ያለፉት ፈርዖን ሰዋጀንሬ»፣ «ያለፉት ፈርዖን ነፈርካሬ»፣ «አህሞስ»ና «ቢንፑ» ይጠቀሳል። በአንድ መላ ምት፣ ከጥንታዊ ምስል ተቀድቶ ፈርዖን ነቢሪራው ሰዋጀንሬ፣ ልጁም 2 ነቢሪራው ነፈርካሬ፣ እና በዘመኑ የኖሩት ልዑላን መስፍኖች አህሞስና ቢንፑ ይጠቀሳሉ። ሆኖም የ2 ነቢሪራው ስም በቶሪኖ ቀኖና ብቻ ስለሚገኝ ሌላ ስሙ አይታወቅለትም።


ቀዳሚው
መንቱሆተፒ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1635-1614 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
2 ነቢሪራው