መደብ:የትራንስፖርት ሚኒስቴር

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ከተደራጁት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል አንዱ ሲሆን በሀገሪቷ ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ስለሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች በበላይነት ሆኖ የሚመራ ተቋም ነው። ይህንንም እንዲያሳካ የሬጉላቶሪ፣ የመሰረተልማት ግንባታ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን በተለያዩ የመጓጓዣ ዘዴዎች መሰረት በማድረግ የሚያከናውኑ ቴክኒካዊ አስፈጻሚ ተቋማት በስሩ አሉት። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣ የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን፣ የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት፣ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር፣ የኢንሹራንስ ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ።

የመደብ (ካቴጎሪ) «የትራንስፖርት ሚኒስቴር» ይዞታ ፦

ይኸው መደብ የሚከተለውን መጣጥፍ ብቻ አለው።