መግነጢሳዊ ስሜን ዋልታ

ከውክፔዲያ
የዋልታ ጉዞ እስከ 2007 ዓም ድረስ፤ አሁንም ከዚህ ግመት ይልቅ ዕጅግ ፈጥኗል።

መግነጢሳዊ ስሜን ዋልታ ማለት የመሬት መግነጢሳዊ ኃይል መስክ በቀጥታ ወደ ታች የሚስብበት ሥፍራ ነው። በስሜን ዋልታ አካባቢ ይዞራል። ጠድከልን ስለሚስብ የስሜን አቅጣቻ ለማጠቆም አገልግሏል። ተዘዋዋሪ እንደ ሆነ ሁሉ ለብዙ ክፍለዘመናት በስሜኑ ካናዳ ይገኝ ነበር። ዳሩ ግን በቅርቡ ባለፉት ዓመታት ካናዳን ትቶ በፍጥነት ወደ ሳይቤሪያ እየተጓዘ ነው። ይህ በምድሪቱ መሃል ያሉት ፈሳሽ ብረታብረቶች አቀማመጣቸውን እየተቀየሩ ስለ ሆነ ነው ይባላል።

እንዲሁም መግነጢሳዊ ደቡብ ዋልታ ባለፉት ቅርብ አመታት ከአንታርክቲካ ወጥታ ትንሽ ወደ አውስትራሊያ ቀርባለች።