ሙአለ ንዋይ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ሙአለ ንዋይ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ካፒታልን ከሞላ ጎደል ረዘም ላለ ጊዜ በኢንዱስትሪ፣ በትራንስፖርት፣ በግንባታና በመሳሰሉት የኢኮኖሚ መስኮች የማዋል ክንዋኔ ነው።

ሙአለ ንዋይ በሁለት ይከፈላል። እነሱም የገንዘብ ሙአለ ንዋይ እና እውን ሙአለ ንዋይ ናቸው። የገንዘብ ሙአለ ንዋይ የሚባለው ለአክሲዮኖችና ለሌሎች የዋስትና ሰነዶች ግዥ የሚውል ካፒታል ሲሆን እውን ሙአለ ንዋይ ደግሞ ለሕንፃዎች፣ ለልዩ ልዩ ማሽኖችና ለመሳሰሉት ቋሚ ንብረቶች ግዥ የሚውለው ካፒታል ነው።

ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]