Jump to content

ታገስ ማሎት

ከውክፔዲያ
(ከማሎት ታገስ የተዛወረ)

ታገስ ማሎት ወይም ማሎት ታገስ ጣልያናዊው መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ በ1490 ዓ.ም. ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በጣልያን ሀገር የነገሠ ንጉሥ ነበር። የአውሩኑስ ልጅ ይባላል። በ2118 ዓክልበ. አውሩኑስ ከቲቤር ወንዝ ደቡብ ባለው ክፍል ገዥ («ኮሪቱስ») ሾመው። በ2117 ዓክልበ. አውሩኑስ ሲሞት ማሎት ታገስ የስሜን ጣልያ («ራዜና») ንጉሥ ሆኖ ተከተለው።

በ2110 ዓክልበ. አካባቢ የፋይጦን መርከቦችና ሕዝቡ ወደ ማሎት ታገስ ወደ ራዜና ደርሰው አውሶናውያንን በጣልያን ምሥራቅ ክፍል፤ የካምና የጋሜርም ልጆች ወዘተ. በሌሎቹ ክፍሎች አገኝተው፣ ከኤሪዳኑስ (ፖ ወንዝ) ስሜን እንዲኖሩ መሬት ተሰጡ።

በ2092 ዓክልበ. ግድም ሦስት ሥፍራዎች በጣልያን አገር በእሳት ተቃጠሉ፦ በዳኑብ ወንዝ አጠገብ፣ በኩሜ እና በደብረ ቬሱቭዩስ። እነዚህ 3 ሥፍራዎች ከዚያው ወዲያ «ፓሌንሳና» እንደ ተባሉ ይህም «የተቃጠሉ ሠፈሮች» መለት እንደ ነበር ይጨምራል። በ2079 ዓክልበ. ግድም ፋይጦን ልጁን ሊጉር በጣልያን ትቶ ወደ ኢትዮጵያ እንደ ተመለሰ ይለናል። ማሎት ታገስም ለፋይጦን የያኑስ የተቀደሱ ሥርዐቶች አስተምሮ ፋይጦን ይህንን በኢትዮጵያ ሠራ ይለናል። በስሜን ጣልያን እስካሁን ሊጉርያ የተባለው አገር ስሙን ከፋይጦን ልጅ ሊጉር ብሔር እንደ ወረሰው ይጨምራል። በ2075 ዓክልበ. ግድም ማሎት ታገስ ሞተና ልጁ ሲካኑስ ተከተለው።

ቀዳሚው
አውሩኑስ
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ
2117-2075 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሲካኑስ