ሲካኑስ (የማሎት ታገስ ልጅ)
Appearance
ሲካኑስ ጣልያናዊው መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ በ1490 ዓ.ም. ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በጣልያን ሀገር የነገሠ ንጉሥ ነበር። የማሎት ታገስ ልጅ ይባላል። የቬቱሎኒያ ክፍል ለሲካኑስ አንደ ተሰየመ ይጨምራል። በርሱ ዘመን የፋይጦን ልጅ ሊጉር ሠፈረኞች ከኤሪዳኑስ (ፖ ወንዝ) አና ከኢስተር (ዳኑብ ወንዝ) መካከል ወዳለው ክፍል አንደ ላከ ይጽፋል። ከዚያ ሲካኑስ የቀድሞ ጣልያን ንጉሥ ያኑስ ሚስት ኣሬቲያ ወይም ሆርቺያ ለማክበር ኣምልኮቷን መሠረተ።
ከቲቤር ወንዝ ደቡብ የኖሩት ታላላቅ ሰዎች ወይም ጊጋንቴስ ወገን ተነሣ። ከሲካኑስ በኋላ ዔናቂ ሉኪ የሚባሉ ኣምባገነኖች ጣልያንን በግፍና ጭቆና ኦሲሪስ አፒስ አስካስወጣቸው ድረስ አንደ ገዙ ይጻፋል።
ቀዳሚው ማሎት ታገስ |
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ 2075-2045 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ) |
ተከታይ ዔናቂ ሉኪ (ኣምባገነኖች) |