የጣልያን ገዢዎች ዝርዝር
Appearance
ማስታወሻ፦ እነኚህ ንጉሦች በድሮ (በተለይ 16ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም.) በአንዳንድ የታሪክ ጸሐፍት የተቀበሉ ሲሆን፣ በአሁኑ ዘመን ሊቃውንት ግን እንደ ታሪካዊ ነገሥታት አይቆጠሩም።
- ኖኅ - 23 ዓመት ከባቢሎን ግንብ ውድቀት በፊት በጣልያን አገር እንደ ሠፈረ ይባላል፤ ለ33 ዓመት ቆየ።
- ኮሜሩስ ጋሉስ (ጋሜር) - 10 ዓመት ከባቢሎን ግንብ ውድቀት በኋላ ንጉሥ ሆነ፤ 63 ወይም 58 አመት ገዛ።
- ኦኩስ ወዩስ - የጋሜር ልጅ፤ 50 ዓመት
- ካሜሴኑስ (ካም) - ከአፍሪካ መጥቶ ጣልያንን ያዘ፤ በዚያ መጥፎ ጸባይ አስተማረ። ከማየ አይኅ ያመለጠችው ጥቁር ሚሥቱን ትቶ የራሱን ዕህት የኖህ ታናሽ ልጅ ሬያን አግብቶ የታላላቅ ሰዎችን ዘር ወለዱ። 19 ዓመት
- ያኑስ - የኖህ 4ኛው ወንድ ልጅ፤ ካምን ከጣልያን ወደ ሊቢያ አባረረውና ጻድቃንን ልጆች (በቲቤር ወንዝ ስሜን) ከተዛቡ ልጆች (በቲቤር ደቡብ) ያስለያቸው ጀመር። 82 ዓመት።
- ክራኑስ ራዜኑስ - የያኑስ ልጅ፣ ከቲቤር ስሜን ገዛ - 54 ዓመት።
- አሩኑስ - 43 ዓመት
- ታገስ ማለት - 42 ዓመት
- ሲካኑስ - 30 ዓመት
- ከታላላቆች ወገን አንዳንድ አምባ ጋኔን ገዙ፣ 30 አመት
- ኦሲሪስ አፒስ (የግብጽ ንጉሥ) አምባ ጋኔኖች አባረራቸው፣ 10 አመት ገዛ
- ሌስትሪጎን - 45 ዓመት
- ሄርኩሌስ ሊቢኩስ - 30 ዓመት
- ቱስኩስ - 27 ዓመት
- አልቴዩስ - 7 ዓመት
- ሄስፔሩስ - 11 ዓመት
- ኢታሉስ ኪቲም (አትላስ) - 19 ዓመት
- ሞርጌስ - 1857-1837 ዓክልበ. ግ.
- ካምቦብላስኮን - 1837-1804 ዓክልበ. ግ.
- ያሲዩስ ያኒጌና - 1804-1758 ዓክልበ. ግ.
- ኮሪባንቱስ
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |