Jump to content

ሌስትሪጎን

ከውክፔዲያ

ሌስትሪጎን ወይም ሌስትሪጎ ጣልያናዊው መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ በ1490 ዓ.ም. ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በጣልያን ሀገር የነገሠ ንጉሥ ነበር። የኦሲሪስ አፒስ ልጅ ኔፕቱን ልጅ ይባላል። ደግሞ ከረጃጅም ሰዎች (ጊጋንቴስ ወይም ኩሬቴስ) ወገን ነበር። ኦሶሪስ ወደ አገሩ ወደ ግብጽ በተመለሠበት ወቅት ሌስትሪጎንን በጣልያ መንግሥት ላይ እንደ ተወው ይለናል። እንዲሁም የኦሶሪስ ሌሎች ረጃጅም አገረ ገዦቹ ቡሲሪስፊንቄ (ከነዓን) ላይ፣ ቲፎን በፍርግያ (ማዮንያ) ላይ፣ አንታዮስሊብያ ላይ፣ ፫ቱ ሎምኒኒኢቤሪያ ላይ እና ሚሊኑስቀርጤስ ነበሩ።

ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የኦሲሪስ ወንድም ሌላው ቲፎን ኦሲሪስን በግብጽ ገደለው። ያንጊዜ የኦሲሪስ ልጅ ሄርኩሌስ ሊቢኩስ ተነሣና ቂሙን በቅሎ ቲፎንን ገደለው። ከዚያ በኋላ በ2002 ዓክልበ. ግድም ሄርኩሌስ ግብጽን ትቶ በየአገሩ ዞሮ እነዚህን ዓመጸኛ አገረ ገዦች ከከነዓን፣ ከማዮንያ፣ ከቀርጤስ፣ ከሊብያና ከኢቤርያ አስወጣቸው። ከዚያ በኋላ ለ፲ ዓመታት በሌስትሪጎን ላይ በጣልያን ጦርነት ሠራ። በ1992 ዓክልበ. ግድም ሌስትሪጎንን ገድሎ ሄርኩሌስ እራሱ የጣልያን ንጉሥ ሆነ።

ግሪክ አፈ ታሪክ ደግሞ ሌስትሪጎናውያን የተባለው ጭራቅ የረጃጅም ሰዎች ጎሣ በጥንት በሲኪልያ ይኖር ነበር። በግሪኩ ትውፊቶች እነዚህ ከሄርኩሌስና በኋላ ከኦዲሴውስ ጋራ ይታግሉ ነበር።

ቀዳሚው
ኦሲሪስ አፒስ
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ
2009-1992 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሄርኩሌስ ሊቢኩስ