አንታዮስ

ከውክፔዲያ
አንታዮስና ሄራክሌስ ሲታገሉ፣ የ520 ዓክልበ. ስኒ

አንታዮስ (ግሪክኛ፦ Ἀνταῖος) በጥንታዊ ግሪክሊብያ አፈ ታሪክ በሊብያ የተገኘ ታላቅ ትግለኛ ሰው ነበር። የፖሠይዶንጋያ ልጅ ይባላል።

እንደ ትውፊቱ የሚያልፍበትን መንገደኛ ሁሉ ለትግል ውድድር ይደፍር ነበር። ከገደላቸው በኋላ ጭንቅላታቸውን በክምችት ላይ ያኖራቸው ነበር። እናቱ የምድር አምላክ «ጋያ» ስለ ነበረች፣ ምድሪቱን እየነካ ሰውነቱ ከሌላ ሰው ኃይለኛ ነበር። ከምድር ላይ በአየር ውስጥ ቢነሣ ግን እንደ ሌላ ሰው ድካም ነው። ስመ ጥሩው ተዋጊ ሄራክሌስ በደረሰ ጊዜ በመጀመርያ ወደ ምድር ጥሎት ሲሆን እናቱ ሆና እንደገና አበረታች። ሄራክሌስ ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምስጢሩን አውቆ አንታዮስን በማቀፍ ጨመቀውና ከምድር አነሣው። ያን ጊዜ ብርታቱ ተወውና ሊገደል ቻለ።

በሌሎች መዝገቦች ዘንድ አንታዮስ የሊብያ ንጉሥ ወይም (እንደ ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ) የሊብያ አገረ ገዥ በሄራክሌስ አባት ኦሲሪስ አፒስ ዘመን ነበር።