ማማ

ከውክፔዲያ

ማማ ከማሣ ውስጥ አዘዕርትን ከአራዊት ለመጠበቅ የሚሰራ አነስተኛ ጎጆ ነው። ይህ ቤት ከፍ ተደርጎ የሚሰራ ሲሆን ለአዳር ጥበቃ አመች ነው። ከዚህ ቤት ለመውረድም ሆነ ወደ ማማው ለመውጣት መሰላል መሳይ መወጣጫ ይሰራለታል። ይህ ቤት የሚያገለግለው አዝዕርቱ ለምግብነት ዝግጁ ከሆኑበት ጊዜ እስከሚሰበሰቡበት ወቅት ብቻ ነው።