ማባዛት

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ማባዛት ማለት ከመደመርመቀነስማካፈል ጋር እንደ አራቱ መሰረታዊ የቁጥር ሂሳብ ስሌቶች የሚታይ ነው። ስራውም አንድን ቁጥር በሌላ ቁጥር ማብዛት ነው።

የማባዛት ምልክት.

የጥንቱ የኢትዮጵያውያን ዘዴ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲሰራበት የነበረው የማባዛት ዘዴ በምሳሌ እንሆ።

12ን በ13 ለማባዛተ ከፈለግን እንዲህ እናረጋለን፡-

12*13 አንደኛውን ቁጥር በ2 ካበዙ በኋላ ሌላኛውን ደግሞ በ2 ያካፍላሉ፣ ተካፍሎ የቀረውን ይተውታል

በሁለት ማብዛት..... በሁለት ማካፈል
12  ................13
24  .................6
48  .................3
96  .................1

ከዚያ በቀኝ በኩል በሚገኙት የማይካፈሉ (odd) ቁጥሮች ትይዩ ያሉትን የግራ ቁጥሮች ይደምራሉ። በምሳሌያችን ላይ እንደሚታየው 13፣ 3 እና 1 በቀኝ የማይካፈሉ ቁጥሮች ሲሆኑ፣ በነሱ ትይዩ ያሉትን ስንደምር 12+48+96= 156

ይህ ዘዴ ለኮምፒውተር ስራ አገልግሎት በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይቻላል ምክንያቱም ከባይናሪ የቁጥር ስርዓት ጋር ተዛማጅነት ስላለው።