Jump to content

ማካ ሞንግ ሩዋድ

ከውክፔዲያ

ማካ ሞንግ ሩዋድ (ማካ ቀይ ጽጉር) በአየርላንድ አፈ ታሪክ ከ440 እስከ 426 ዓክልበ. ድረስ የአይርላንድ ብቸኛ ከፍተኛ ንግሥት ነበረች።

የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት፣ ከ503 ዓክልበ. ጀምሮ (ድሮ አቆጣጠር) የማካ አባት አይድ ሩዋድዲጦርባ እና ኪምባይጥ በስምምነት እያንዳንዱ ዙፋኑን በየ፯ቱ ዓመታት እንዲፈራርቁ ወሰኑ። እንዲሁም ሦስቱ ነገሥታት እያንዳንዱ ለ፫ ጊዜ የ፯ ዓመታት ዘመኖች ነበሩዋቸው፤ ይህም 63 ዓመታት ፈጀ። (በሌቦር ጋባላ ኤረን በአንዱ የድሮ ግጥም ያ ከክርስቶስ ልደት 450 ዓመታት በፊተ እ.ኤ.አ. ወይም 458 ዓክልበ. አካባቢ እንደ ነበር ያረጋግጣል።)

አይድ ሩዋድ ግን ዓርፎ እንደገና ፈንታው በደረሰበት ወቅት በ440 ዓክልበ. ሴት ልጁ ማካ ሞንግ ሩዋድ ስለ ዙፋኑ ይግባኝ አለች። ይች ማካ ዲጦርባን በውግያ ገደለች፣ የተረፈውንም ንጉሥ ኪምባይጥን አገባችው። ከዚያ ኪምባይጥና ማካ አብረው ለ፯ ዓመታት ነገሡ፤ ኪምባይጥም በ433 ዓክልበ. አርፎ ከፍተኛ ንግሥት ማካ ለብቻዋ ሌላ ፯ አመታት ነገሠች። በ426 ዓክልበ. ሬክታይድ ሪግዴርግ ገደላትና ለንጉሥነቱ ተከተላት።