ማዕቀብ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ

ማዕቀብፖለቲካና የኢኮኖሚ እገዳ ሲሆን ሕጋዊ በሆነ ውሳኔ ኃይል ተጠቅሞ አንድን ሰው፣ ሀገር ወይም ተቋም ከያዘው አፈንጋጭ አስተሳሰብ ወይም ድርጊት እንዲመለስ፣ የሚጠበቅበትን መስመር እንዲከተል ወይም ለትክክለኛው ሕግ ተገዥ እንዲሆን ለማድረግ በፖለቲካና በኢኮኖሚ እገዳ አማካይነት የሚወሰን ቅጣት ነው። ይህ ዓይነቱ ቅጣት በተለይ የሚጣለው ዓለም አቀፋዊ ውሳኔዎችን በማያከብር ወገን ላይ ሲሆን በሙሉ ተፈጻሚነት ሊያገኝ የሚችለው የውሳኔው ደጋፊዎች ቅጣቱ ከተጣለበት ወገን ጋር ያላቸውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ግንኙነት ሲያቋርጡና እንዲሁም ሕገወጥ ድርጊቱን በማንኛውም ቦታና ጊዜ በማጋለጥና በማውገዝ ነው።

ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]