ምሻምሾ

ከውክፔዲያ

ምሻምሾ በኢትዮጵያ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ነው። በ1902 ዓ.ም በታተመው የትብብር ሥራቸው፣ አለቃ ታየ ሚሻ ሚሾ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅላት ለማስታዎስ በስቅለት ቀን፣ በዓመት ኣንድ ጊዜ እንደሚካሄድ ያሰፍራሉ። [1] እንደርሳቸው አባባል፣ ሚሻ ሚሾ እሚለው ሃረግ የመጣ ውሾ ዉሾ ከሚል ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ ከተሰነዘረ ስደብ ትውስታ ነው።

የበዓሉ ትውፊት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሕጻናት ሚሻ ሚሾ ብለው አንድ ቤት ሲጨፍሩ፣ ከቤቱ ዱቄት፣ አዋዜ፣ ቅባ ኑግ ወይንም ጬው እንዲሰጣቸው በመጠበቅ ነው። ይህን ያገኙ እንደሆን፦ «ዕድሜ የማቱሳላን ጽድቅ የላሊበላን ይስጥለነ።» ብለው መርቀው ይሄዳሉ። ከተነፈጉ ደግሞ፦ «እንደ ሰፌድ ይዘርጋሽ፣ እንደ ማጭድ ይቆልምሽ፤ ቁመት ያውራ ዶሮ፣ መልክ የዝንጀሮ፤ ግማት የፋሮ ይስጥሽ። » ብለው ተራግመው ይሄዱ እንደነበር አለቃ ታየ ትውፊቱን አስቀምጠዋል[2]

በአሁኑ ዘመን ከሚቀነቀኑ ዜማዎች ውስጥ ይሄ ይገኝበታል፦

ወይ ሚሻ ሚሾ፣
ሚሻ ሚሾ፣
አንድ አውራ ዶሮ፣
እግሩን ተሰብሮ፣
እሜቴ፣ ይነሱ፣
ጉስጉሳ ይዳብሱ።

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Mittwoch, Eugen, 1876-1942. Abessinische Kinderspiele. Berlin: Gedruckt in der Reichsdruckerei, 1910. ገጽ ፲፪
  2. ^ https://babel.hathitrust.org/cgi/pt?id=mdp.39015049010567;view=1up;seq=16