Jump to content

ሞንተምሳፍ

ከውክፔዲያ

==

ጀዳንኽሬ ሞንተምሳፍ
«ጀዳንኽሬ» የሚል ጥንዚዛ
«ጀዳንኽሬ» የሚል ጥንዚዛ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1594 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ 1 ደዱሞስ ?
ተከታይ መራንኽሬ 6 መንቱሆተፕ
ሥርወ-መንግሥት 16ኛው ሥርወ መንግሥት

==


ጀዳንኽሬ ሞንተምሳፍላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1594 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ የሚታወቅ «ጀዳንኽሬ» ከሚሉ ሁለት ጥንዚዛዎችና አንድ ነሐስ መጥረቢያ፣ እንዲሁም «ጀዳንኽሬ ሞንተምሳፍ» ከሚል ድንጋይ ነው።

ቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ ከሰኸምሬ ሸድዋሰት ቀጥሎ አምስት የፈርዖን ስሞች ጠፍተዋል። በአቶ ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ ሞንተምሳፍ በነዚህ አምስት መካከል ነበሩ።

ቀዳሚው
ሰኸምሬ ሸድዋሰት
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1594 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
መራንኽሬ 6 መንቱሆተፕ