ሠርጣን

ከውክፔዲያ
የባሕር ሸርጣን

ሠርጣን ወይም ሸርጣን በባሕር ወይም በየብስ የሚገኝ በጋጥመ-ብዙ ክፍለ ስፍን ውስጥ የሚገኙት ፍጡሮች ናቸው። እንደ ዛጎል ቢኖራቸውም የዛጎል ለበስ ክፍለስፍን አይደሉም።

ሸርጥ ዓሣ ክፍለመደብ ውስጥ 93 አስተኔዎችና 6,793 ዝርዮች አሉዋቸው። ከነዚህ 850 ያህል ዝርዮች በየብስ ይኖራሉ።

ባሕታዊ ሠርጣን የተባለው አስተኔ የራሱን ዛጎል ስለሌለው በማናቸውም ወና ባዶ ዛጎል ውስጥ ይኖራሉ፤ ይህም ባይገኝም በቆሻሻ ውስጥ ይኖራሉ።

በብዙ አገሮች የሠርጣን ስጋ ይበላል፤ በሕገ ሙሴ ይከለክላልና በተለይ በአይሁድና እንዲሁም በሺዓ እስልምና የማይበላ እንስሳ ነው።