ሥነ ግራፍ

ከውክፔዲያ
የግራፍ ምስል

ሥነ ግራፍሒሳብ ትምህርት አካል ሲሆን የሚያጠናውም ግራፍ የሚሰኙ የሒሳብ መዋቅሮችን ነው። እዚህ ላይ ግራፍ ሲባል የሁለት ጥንድ ነገሮችን ዝምድና የሚወክል ጽንሰ ሐሳብ ነው። ግራፍ እንግዲህ የጉብሮችና ጉብሮችን የሚያገናኙ ጠርዞች ስብስብ ነው። ሁም ግራፎች በሁለት ይከፈላሉ፣ እነርሱም አቅጣጫዊ እና ኢአቅጣጫዊ ናቸው። ኢአቅጣጫዊ እሚባለው በአንድ ጠርዝ ላይ ያሉ ሁለቱ ጉብሮች አንዳቸውን ከሌላው የሚለያቸው ነገር ሳይኖር ሲቀር ነው። ለምሳሌ ሁለት ሰዎች ቢጨባበጡ፤ ሰውየ ሐ ሰውየ መ ን መጨበጡ ሰውየ መ ሰወየ ሐን ከመጨበጡ ጋር ምንም ልዩነት የለውም ።ስለሆነም ሐ ና መን እንደጉብር ብንወስድና መጨባበጣቸውን እንደ ጠርዝ ብንስል፤ የምናገኘው ግራፍ ኢአቅጣጫዊ ይሰኛል ማለት ነው። በዚህ ተቃራኒ አቅጣጫዊ ግራፍ ሁለቱን ጉብሮች ይለያል። ስለዚህም ግራፉ ከአንዱ ጉብር ወደ ሌላው የተሰነዘረ ነው እንላለን። ለምሳሌ በአንድ ድግስ ውስጥ አበበን መሰረት ብታውቀው፤ የርሷ እርሱን ማወቅ የግዴታ እርሱ እሷን ያውቃታል ማለት አይደለም። ስለሆነም ግራፉ ከመሰረት ወደ አበበ ይተሰነዘረ አቅጣጫዊ ግራፍ ነው እንላለን።