Jump to content

ሩስድክ

ከውክፔዲያ


ሩስድክ የሚለው መጠሪያ ስማችን ምህንፃረ ቃል ሲሆን “የሩሃማ ስነ-ጽሑፍና ድራማ ክበብ” ማለት ነው። ይህንን ስም የመረጠነው ደግሞ እኛ በዘመናችን በዘመኑ በመጨረሻ ዘመን የምንኖር ስንሆን የሰው ልጅ በተፈጥሮው ለአመጽ፣ ለኃጢአት እና እግዚአብሔርን በማይታዘዙት ትውልድ መካከል ስለሚንኖር ምህረትን ለትውልድ፤ ምህረትን ለቤተ ክርስቲያን ተመኝተን ሩሃማ አልን! ሩሃማ ማለት “ምህረት የሚገባት” ማለት ነውና።

ይህንን ሩስድክ የሚለውን መጠሪያ ስም የመረጠንበት ምክንያት እኛ አሁን ያለነው በመጨረሻ ብቻ ሳይሆን በመጨረሻ መጨረሻ ላይ ስንሆን የሰው ልጅ በተፈጥሮው ለአመጽ፣ ለኃጢአት እና [እግዚአብሔር]ን በማይታዘዙት ትውልድ መካከል ስለሚንኖር ምህረትን ለትውልድ፤ ምህረትን ለ[ቤተ ክርስቲያን] ተመኝተን ሩሃማ አልን! ሩሃማ ይሁንልን! ሩሃማ ማለት ምህረት የሚገባት ማለት ነውና።

ሩስድክኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንደቡብ ምእራብ ቀጣና በማሌ አጥቢያት ቤተ ክርስቲያናት ኅብረት በኮይቤ አጥቢያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በ2003 ዓ/ም በአቀፋ አየለማህተም ታድዮስ እና ዘገዬ ላሌ አማካኝነት የተደራጀ የስነ-ጽሑፍና ድራማ ክበብ ሲሆን፤ ከ2003 ዓ/ም አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዓላትን ጨምሮ ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ የስነ-ጽሑፍድራማ እና ሌሎች አዳድስ የአርት ሥራዎችን በመሥራት በየዓመቱ ለወንጌል ሥርጭት በመውጣት በመስበክና ከሌሎች አጥቢያት ጋር ትስስር በመፍጠር በየአጥቢያቱ በመሄድ እያገለገለ ያለ የስነ-ጽሑፍና የድራማ ቡድን ነው።

አሁን ደግሞ በዚህ ሩስድክ ዊኪ ላይ በሩስድክ አማካኝነት የተሠሩ ሥራዎችን፣ በዝግጅት ላይ ስላሉ እና በቅርቡ በመድረክና በቪድዮ ሊቀርቡ ያሉትን ሥራዎችን ጨምሮ ተከታታይ ድራማዎችን፣ ጽሑፎችን፣ እና ሌሎች ሥራዎችንና ወቅታዊ ዜገባዎችን ከሩስድክ ዜና መጽሔት ታገኛላችሁ።