ሩድራይጌ ማክ ሲጥሪጊ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ሩድራይጌ ማክ ሲጥሪጊአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ111 እስከ 81 ዓክልበ. ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።

አብዛኞቹ የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት የሩድራይጌ ዘመን ለ70 ዓመታት ቆየ፤ ጥቂቶች ግን 30 ዓመት ይላሉ። የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብሮ) በመከተል፣ ይህ እስከ78 ዓክልበ. ድረስ ይሆናል። (በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።) ዘመኑ 30 ዓመት ከሆነ፣ በተረፈ በሌቦር ጋባላ ኤረን እንደሚለው ኮብጣክ ኮኤል ብሬግ በ314 ዓክልበ. እንደ ሞተ ይስማማል።