ሮቃ

ከውክፔዲያ
ሆማር / ሮቃ

ሆማርሆመር፣ ወይም እንደ ኦሮምኛ ሮቃ (Tamarindus indica) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ዛፍ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እስከ 15 m. የሚደርስ ሁሌ ለም ነው።

ፍሬው በውስጡ ዘሮቹ አሉት።

አስተዳደግ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዘሮቹ ጉንቆል ለማድረግ ለአጭር ጊዜ ሊፈሉ ይቻላል። ከዚያ ደረቅ ቢቆዩ ለጥቂት ወሮችም ረቢ ይሆናሉ።

ዛፉ ረጅም ሕይወት አለው፣ በ3 ወይም 4 አመት ውስጥ ያፈራል።

ፍሬው ቡናማ ወይም ቀይ-ቡናማ ሲሆን ይመረታል። አንድ ዛፍ ብቻ በየዓመቱ 1.75 ኩንታል ፍሬ ሊሰጥ ይችላል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በእርጥብ ቆላ ደኖች፣ በወንዝ ዳሮች፣ በጉንዳን ጎጆች መኃል፣ ከ 800-1600 m ከፍታ ይገኛል።

በአፍሪካና በየመን በዱር ኗሪ ተገኝቷል፣ በተረፈውም አለም ተለምዷል።

የተክሉ ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በተለይ በሕንድ በሌሎችም አገራት እንደ ሰብለ ገበያ ይታደጋል።

ፍሬው ጥሬ ሲሆን ደግሞ ይበላል። ፍሬው በአለም ዙሪያ በብዙ አይነት ጣፋጭ አበሳሰል ውስጥ ይገኛል። በላቲን አሜሪካ አንድ መጠት «ታማሪንዶ» ከተፈላው ፍሬ ይሠራል።

ፍሬውም እንደ አቀዝቃዥ፣ ምግብ ፈጪ፣ በሆድ መነፋት ላይ፣ ለሚያስቀምጥ መድሃኒት፣ በእስኩርቪም ላይ ይጠቀማል።

ፍሬው ከሞከከ ስለ አሲዱ መዳብንም ሆነ ነሐስን ለማጽዳት ይስማማል።

በሎሚ ጭማቂ ፈንታ የሆማር ጭማቂ ቅዝቃዛ መጠት ይሆናል። በአስመራ የደረቀው ፍሬ እና ጭማቂው በሱቅ ተገኝተው ነበር።

እንጨቱ ለከሰል ማለፊያ ነው።

ቅጠሎቹ ከፍ ያለ አሲድ አለባቸው፣ በብጉንጅ ላይ እንደ አምቅ ያገልግላሉ። የውስጡ ዘሮቹም በተቅማጥ ተጠቅመዋል።

ዘይቶቹ በአየሩ ተናኝ ስለሆኑ፣ በዛፉ ጥላ መቀመጥ የሚያረጋ ውጤት እንዳለው ተዘግቧል።[1]

በሌሎችም አገራት ፍሬው ለሆድ ድርቆት እንደሚያስቀምጥ መድሃኒት ታውቋል።.[2][3]

በደቡብ-ምሥራቅ እሥያ፣ የቅጠሉም አምቅ በግንባሩ ለትኩሳት ማከሙ ይታወቃል።

ናይጄሪያ በተደረገ 1998 ዓም ጥናት፣ ሆማር ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪዮች እንዳሉት ተረጋገጠ።[4]

  1. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ Havinga, Reinout M.; Hartl, Anna; Putscher, Johanna; Prehsler, Sarah; Buchmann, Christine; Vogl, Christian R. (February 2010). "Tamarindus Indica L. (Fabaceae): Patterns of Use in Traditional African Medicine". Journal of Ethnopharmacology 127 (3): 573–588. doi:10.1016/j.jep.2009.11.028. PMID 19963055. 
  3. ^ Panthong, A; Khonsung, P; Kunanusorn, P; Wongcome, T; Pongsamart, S (July 2008). "The laxative effect of fresh pulp aqueous extracts of Thai Tamarind cultivars". Planta Medica 74 (09). doi:10.1055/s-0028-1084885. 
  4. ^ Doughari, J. H. (December 2006). "Antimicrobial Activity of Tamarindus indica". Tropical Journal of Pharmaceutical Research 5 (2): 597–603. doi:10.4314/tjpr.v5i2.14637. http://ajol.info/index.php/tjpr/article/view/14637/2742.