ሰባት
Appearance
ሰባት በተራ አቆጣጠር ከስድስት የሚከተለው ቁጥር ነው።
ምልክቱ ከግዕዝ እንደ ተወረሰ ፯ ነው፣ ይህም ከግሪክ አልፋቤት ፊደል ዜታ (በትንሹ «ζ») እንደ ተወሰደ ይታመናል።

በብዙ ልሳናት የሚገኘው ምልክት 7 ከሕንዳዊ ቁጥር ምልክቶች ተደረጀ። እነዚህ ምልክቶች በአውሮፓ ከ968 እና 1550 ዓም መካከል እየተደረጁ ተቀባይነት አገኙ። ከዚያ አስቀድሞ በሮማውያን ቁጥር ምልክቶች የ«ሰባት» ምልክት «VII» (ወይም vij) ነበር።
| ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |