ቁጥር

ከውክፔዲያ

ቁጥር ፦ ለመቁጠር ወይም ደግሞ ለመለካት የምንጠቀምበት የሂሳብ ቁስ ነው። ቁጥሮች ከዚህ ከሁለቱ ጥቅማቸው ውጭ በአሁኑ ጊዜ ለልዩ ልዩ ጥቅም ይውላሉ። ለምሳሌ፦ አንድን ነገር ለመለየት (ምሳሌ ስልክ ቁጥር)፣ ለመደርደር (ሲሪያል ቁጥር)፣ ኮድ ለማበጀት (ISBN ቁጥር) ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው።

አንድንድ ሂደቶች አንድ ወይም ሁለት ቁጥሮችን ወስደው ሌላ ቁጥርን ይሰጡናል። እኒህ ሂደቶች ኦፕሬሽን ይባላሉ። ለምሳሌ ቁጥር ሲስጠን ቀጣዩን ቁጥር የምናገኝ ከሆነ ይህ ሂደት ቀጣም በመባል ይታወቃል፣ የሚወስደውም ቁጥር ብዛት አንድ ብቻ ስለሆነ ዩናሪ ኦፐሬሽን ይባላል። እንደ መደመርመቀነስናማባዛትማካፈል ያሉት ደግሞ ባይናሪ ኦፕሬሽን ይባላሉ። እንደዚህ ያሉትን የቁጥር ኦፕሬሽን የሚያጠናው የሂሳብ ክፍል ሥነ ቁጥር ወይም አርቲሜቲክ (በእንግሊዝኛ Arithmetic) ይሰኛል።

የቁጥሮችን ቁመና በግሩፕቀለበትሜዳ የሚያጠናው የሂሳብ ክፍል የነጠረ አልጀብራ ተብሎ ይታወቃል።

ቁጥር አይነቶች
የተፈጥሮ ቁጥሮች 0, 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, ..., n
ኢንቲጀር ቁጥሮች -n, ..., -8, -4, -3, -2, -1, 0, 1, 2, 3, 4, 5, ..., n
ፖዘቲቭ ኢንቲጀሮች 1, 2, 3, 4, 5, ..., n
ራሽናል ቁጥሮች a/b where a and b are integers and b is not zero
እውን ቁጥሮች A rational number or the limit of a convergent sequence of rational numbers
ያቅጣጫ ቁጥሮች a + bi where a and b are real numbers and i is the square root of -1

የቁጥር ምልክቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥሮች ምልክቶች (0123456789) በዘመናዊ ቅርጾቻቸው በአውሮፓ ከ1550 ዓም ግድም ጀምሮ ነው። ከዚያ በፊት በነባሮች ቅርጾቻቸው በአውሮፓ ከ968 ዓም ጀምሮ ይታወቁ ነበር። እነርሱም ከአረብኛ ቁጥሮች ተወሰዱ። አረቦችም የሕንድ ቁጥሮች የበደሩ ከ768 ዓም ጀምሮ ነበር። የአረብ ሊቃውንት ከአውሮፓ ሊቃውንት በነዚህ ፪ መቶ አመታት በዜሮ (0) ጥቅም ቅድምትነታቸው ምክንያት፣ በሥነ ቁጥር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሳይንስ ዘርፎች ሥነ ቁጥሮች በመቀለላቸው በኩል፣ ለጊዜው የአረብ አለም ሊቃውንት በይበልጥ ለመግፋት ቻሉ። ሕንዶችም የዜሮ ጥቅም ያወቁት ቢያንስ ከ620 ዓም ጀምሮ ነበር። ለያንዳንዱ ሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥር ምልክት አደረጃጀት፣ በየአማርኛ ስሙ አንድ ሁለት ሦስት አራት አምስት ስድስት ሰባት ስምንት ዘጠኝ ይዩ።

ግዕዝ ቁጥሮች ምልክቶች በቀጥታ ከግሪክ ፊደል ቁጥሮች ተበደሩ፤ እንዲሁ፦

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 20 30 40 50 60 70 80 90 100
ግሪክኛ Α Β Γ Δ Ε Ϛ Ζ Η Θ Ι Κ Λ Μ Ν Ξ Ο Π Ϙ Ρ
ቅብጥኛ Ϥ
ቢዛንስ α β γ δ ε Ϛ ζ η θ ι κ λ μ ν ξ ο π ϟ ρ
ግዕዝ

ይህ የግሪኮች ዘዴ የተለማ ምናልባት 400 ዓክልበ. ግድም ሲሆን፣ ከዚያ ቀድሞ ሌላ የአቆጣጠር ዘዴ ለግሪኮቹ ነበራቸው። የግዕዝ ቁጥር ቅርጾች ከ500 ዓም ያህል ጀምሮ ናቸው (የአባ ገሪማ ብራናዎች)።

በአውሮፓ ከሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥሮች በፊት የነበረው ዘዴ ሮማዊ ቁጥሮች በአንዳንድ ቦታ እስካሁን ይገኛል። በዚህም፦

  • I = ፩ ፣ II = ፪ ፣ III = ፫
  • IV = ፬ ፣ V = ፭ ፣ VI = ፮ ፣ VII = ፯ ፣ VIII = ፰
  • IX = ፱ ፣ X = ፲ ፣ XI = 11 ወዘተ.
  • XX = ፳ ፣ XXX = ፴
  • XL = ፵ ፣ L = ፶ ፣ LX = ፷
  • XC = ፺ ፣ C = ፻ ፣ CC = ፪፻ ፣ CCC = ፫፻
  • CD = ፬፻ ፣ D = ፭፻ ፣ DC = ፮፻ ወዘተ.
  • CM = ፱፻ ፣ M = ፲፻ ፣ MC = ፲፩፻

እነዚህ ቅርጾች እንደ ላቲን አልፋቤት ፊደላት I, V, X, L, C, D, M ለመምሰል የጀመሩ ከ1 ዓም አካባቢ ነው። ሆኖም በውነት ከጥንታዊ ኤትሩስክኛ ቁጥሮቹ ምልክቶች («𐌠, 𐌡, 𐌢, ⋔, 𐌚, ⊕» ለ«I, V, X, L, C, M») የተለሙ ናቸው።

ከነዚህ ዘዴዎች በቀር በጣም ብዙ ሌሎች የአቆጣጠር ምልክቶች ዘዴዎች ከቦታ ወደ ቦታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለያዩ በሰው ልጆች ታሪክ ላይ ተገኝተዋል።