ሰንሻይን ኮንስትራክሽን

ከውክፔዲያ

ሰንሻይን ኮንስትራክሽንኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉ የኮንስትራክስን ኢንዱስትሪዎች አንዱ ነው። ይህ ድርጅት የተመሰረተው በሚያዚያ 1984 ሲሆን ቀስ በቀስ በ1993 ወደ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያነት ተለወጠ። የድርጅቱ መስራች ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ አርኪቴክት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ ናቸው። ድርጅቱ በሃገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የቤቶችና የመንገድ ስራዎችን በመስራት ይታወቃል። በድርጂቱ ባለቤት ተነሳሽነትም የተለያዩ የእርዳታ አስተዋጽኦዎችን አድርጓል። ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ 1.5 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር የሚጠጋ ካፒታል ያለው ነው።