Jump to content

ሰይጣን

ከውክፔዲያ

ሠይጣንመጽሐፍ ቅዱስና በልዩ ልዩ ሃይማኖት ትምህርት እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው ክፉ ኃይል ነው።

ተዋሕዶ ሃይማኖት ዘንድ፣ የሰይጣኖች አለቃ ዲያብሎስ አመጸኛ ሆኖ እስከ ዕለተ ደይን ድረስ ይታስራል። በዕለተ ደይንም በእግዚአብሔር ምሕረት ያልዳኑ ሰዎች ሁሉ ከዲያብሎስ ጋር በገሐነመ እሳት ሊቀጡ ነው የሚል እምነት ነው። በአብያተ ክርስትያናት ውስጥ ባሉት ስዕሎች ላይ የዲያብሎስ ቅርጽ ቢታይ፣ ሁልጊዜ እጅና እግሩን ታሥሮ በእሳትም ሓይቅ ተቀምጦ በስቃዩ ጮኾ ይሆናል።

ሰይጣን ሌላው ስሙ ዲያብሎስ ነው። ሰይጣን ከመሰይጠኑ በፊት የነበረው ስም ሳጥናኤል ሲሆን በዕብራይስጥ አዛዝኤል ይባላል። "አዛዝ" ማለት "ጥንካሬ" ማለት ሲሆን "ኤል" ማለት አምላክ ማለት ነው፤ "አምላክ ጥንካርዬ ነው" ማለት ነው።

ዕብራይስጥ የ«ሰይጣን» ትርጉም «ተቃዋሚ» ሲሆን የእግዚአብሔርን ዕቅዶች የሚቃወም ማናቸውም መንፈስ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በማቴዎስ ወንጌል 16:23 እና ማርቆስ ወንጌል 8:33 ጴጥሮስኢየሱስ ይህ ያልከው ስቅለትህ አይሁን! ሲለው ኢየሱስ ጴጥሮስንም «ሰይጣን» ይለዋል። አዛዜል የተባለው ከሴት (የአዳም ልጅ) ተወላጆች መካከል ያመጸ ሰው እንደ ነበር በአንዳንድ ልማዶች ይታመናል። ያው ሰይጣን በመጽሐፈ ሄኖክ ዘንድ ፍዳውን አገኝቶታል። ከአዛዜልም በፊት በእባብ ወይም ከአዛዜልም በኋላ ወደፊት ማናቸውም ተቃዋሚ መንፈስ ወይም ሠይጣን እንዲሁም ፍዳውን ያገኛል። በማርቆስ 3:25-26 ኢየሱስ ስለ ሠይጣን እንዳስተማረ «እርስ በርስ የተለያየ ቤት» ሲለው፣ ሰይጣን በራሱ ላይ ተለያይቶ እንደ ሆነ እንጂ ክፉው በአንድ በተዋኸደ ፈቃድ እንደማይመራ ያሳያል።

በአብርሃማዊ ትምህርቶች ዘንድ ሰው ሁሉ ወይም በኅሊና ወይም በትዕቢት እንደየመጠኑ እንዲመራ ነጻ ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ በአንዳንድ ሰዎች እምነቶች ግን አምላኩና ሠይጣኑ በእኩልነት ሃይለኛ ይሆናሉ የሚለው ሀሣብ መጀመርያ በዞራስተር ትምህርቶች እንደ ተገኘ ይባላል።

በአብርሃማዊ ትምህርቶች ደግሞ አምላኩ እንደ ብርሃን ሲሆን፣ ሰይጣን ግን ጉድጓዶች የማይታዩበት ጥላውን ወይም ሌሊት እንደሚመርጥ ይባላል። በአረመኔ ግሪክ አገር ወይም ሮሜ መንግሥት ባሕል ግን፣ ይህን ገልብጠው ክፉው ብርሃኑን የሚያመጣ ይሆናል ስላሉ፣ የሮማይስጥ ስያሜ «ሉሲፈር» («ብርሃን አምጪ») ተቀበለ። ይህ ርዕዮተ አለም በመጽሐፍ ቅዱስ ባይደገፍም፣ የሮማይስጥ ትርጉምና ብዙ የአውሮጳ ትርጉሞች በትንቢተ ኢሳይያስ 14:12 በ«የአጥቢያ ኮከብ» ፈንታ «ሉሲፈር» የሚለውን ስያሜ አስገብተዋል። ንባቡ በኦሪጂናሉ ዕብራይስጥ በሙሉ ሲነበብ ግን «የአጥቢያ ኮከብ» የተባለው የባቢሎን ንጉሥ ፪ ናቡከደነጾር እንደ ሆነ ግልጽ ነው። ስለዚህ ከዚሁ ጥቅስ ሰይጣናዊ መረጃ ደርሷል የሚለው ትምህርት ስሕተት ይመስላል፤ ሆኖም በአንዳንድ ሃይማኖት በተለይም በሞርሞኒስም እንደዚያ ይታመናል።

: