Jump to content

ሱውን ጽዝዕ

ከውክፔዲያ
የዓለቃ ሱውን ዘመናዊ ሃውልት

ሱውን ጽዝዕ 孫子 ከ544 - 496 ዓ.ዓ. በጥንታዊ ቻይና ይኖሩ የነበር የጦር መሪ፣ ውትድርና ስልት ቀያሽ እና ፈላስፋ ነበሩ። በአሁኑ ዘመን ስማቸው እሚነሳ ኪነ ጦርነት የተባለውን መጽሐፍ በመድረሳቸው ነው።

ዓለቃ ሱውን ከዛሬ 25 ክፍለ ዘመናት በፊት የኖሩ ሰው ቢሆንም፣ ሥለ ጦርነት ምንነት እና እንዴት መካሄድ አለበት በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ለየት ያለ አስተያየት በማስቀመጣቸው ዘመናትን ተሻግረው ይወደሳሉ። ጦርነት በጦረኞች ዘንድ እንደ ስፖርት የሚታይ እንዲሁም ከተዋጊዎች ክብር ጋር በጣም የተያያዘ ነበር። ሱውን በተቃራኒ፣ ጦርነት ከልብ የሚያሳስብ ፣ መዘዙ ከፍተኛ የሆነ ነገር እንደሆነ ጽፈዋል። ስለሆነም ጦርነት ከተካሄድ በጠላት ላይ ድል ለማግኘት ብቻ እንጅ ሌላ አላስፈላጊ ግብ ለመታት እንዳልሆነ አስረድተዋል።

ይህ አስተያየት ግልጽ ቢመስልም፣ ነገር ግን ለዘመኑ እንግዳ ነበር። ለምሳሌ፣ ጦርነት «ድልን ለመቀዳጀት» ብቻ መካሄድ ካለበት፣ የግዴታ በሃይል ብቻ መካሄድ የለበትም። ምክንያቱም፣ እንደ ዓለቃ ሱውን አስተያየት፣ በኅሊናዊ ጫና ብቻ የጠላት ሃይል ሊፈረካከስ ይችላልና። በሌላ ጎን፣ ጦርነቶች ብዙ ደም ከማፋሰስ ይልቅ፣ ለአንድ ትንሽ አላማ ብቻ መካሄድ እንዳለበት ያስገነዝባል።

«ኪነ ጦርነት» በጥንዊት ቻይናና አጎራባች አገሮች በጥልቅ የተጠናና በባሕላቸው ዘንድ ሰርጾ የሚገኝ መጽሐፍ ነው። በአሁኑ ዘመን፣ በምስራቅ እስያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ዘንድ፣ ለሥነ ንዋይ፣ ለስፖርት፣ ለወታደራዊ ስልት እና መሰል የተፎካክሮ-ተግባራት ይህ የዓለቃ ሱውን መጽሐፍ ይጠናል።

ከሱውን ጽዝዕ ጥቅሶች፦

«እራሱን እና ጠላቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ መቶ ውጊያዎች ቢያካሂድ አንዱንም አይሸነፍም። እራሱን የሚያውቅ ግን ጠላቱን የማያውቅ፣ በድሎቹ ልክ ሽንፈት ያጋጥመዋል። እራሱንም ሆነ ጠላቱን እማያውቅ፣ ምንም ጊዜም ይሸነፋል።»

ዓለቃ ስውን