Jump to content

ሳቢዩም

ከውክፔዲያ

ሳቢዩም ከ1757 እስከ 1743 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን ፫ኛ ንጉሥ ነበረ። አባቱን ሱሙላኤልን ተከተለው።

በአባቱ ሱሙላኤል ዘመን መጨረሻ ወይም 1757 ዓክልበ. ግድም የላርሳ ንጉሥ ሲን-ኢዲናም ባቢሎንን እንዳሸነፈው በርሱ ዓመት ስም ዘገበ።

ለሳቢዩም ዘመን 14 ያህል የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል። ከነርሱም መካከል፦

1751 ዓክልበ. ግ. - «የላርሳ ሥራዊት በመሣርያዎች የተመታበት ዓመት»
1746 ዓክልበ. ግ. - «የካዛሉ ግድግዳ የጠፋበት ዓመት»

የሳቢዩም ተከታይ ልጁ አፒል-ሲን ነበረ።

ቀዳሚው
ሱሙላኤል
ባቢሎን ንጉሥ
1757-1743 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አፒል-ሲን

የውጭ መያያዣ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]